👉​ለግንባታ ዘርፍ ባለሙያዎች እና አልሚዎች በሙሉ🏗️

​የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን የኮንስትራክሽን ማዕድናት ቁፋሮና አስተዳደርን የሚመራ አዲስ መመሪያ አወጣ። "የኮንስትራክሽን ማዕድን ፈቃድ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 191/2018" የተሰኘው ይህ ሰነድ በዘርፉ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን ያለመ ነው።

🚧​ቁልፍ ነጥቦች፦

​📍 የማዕድን አይነቶች
ጥቁር ድንጋይ፣ ገረጋንቲ፣ ቀይ አሸዋ፣ ቀይ አፈር፣ ነጭ የግንብ ድንጋይ፣ የወንዝ አሸዋ፣ ጠጠር እና መሰል ማዕድናት።

​⏳ የፈቃድ ዘመን
​ጥቁር ድንጋይ፦ እስከ 5 ዓመት (በየዓመቱ ይታደሳል)።
​ገረጋንቲ፣ አሸዋና ነጭ ድንጋይ፦ እስከ 2 ዓመት (በየዓመቱ ይታደሳል)።

​🚫 ክልክል ቦታዎች (ቁፋሮ አይፈቀድም)
​ከመኖሪያ መንደሮችና ኢንዱስትሪ ፓርኮች በ500 ሜትር ራዲየስ ውስጥ።
​ከወንዝ ዳርቻዎች በ30 ሜትር ራዲየስ ውስጥ።

​ከከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች በ25 ሜትር ራዲየስ ውስጥ።

​መቃብር፣ ፓርክ፣ ሃይማኖታዊ ስፍራዎችና ብሔራዊ መታሰቢያዎች አቅራቢያ።

​📋 አልሚዎች ማሟላት ያለባቸው
​የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ (EIA) እና የአዋጭነት ጥናት ማቅረብ።
​ለአካባቢ ጥበቃ ዋስትና የሚሆን የገንዘብ ማስያዣ ማስቀመጥ።

​በየሦስት ወሩ የሥራ አፈጻጸም፣ በየወሩ የገቢ ሪፖርት ማቅረብ።
​የስፋት ማስፋፊያ የሚፈቀደው ቀደም ሲል ከተሰጠው ቦታ 70% ሲያለሙ ብቻ ነው።

​⚠️ ማሳሰቢያ
​ግለሰቦች ለንግድ ላልሆነ የግል ግንባታ በይዞታቸው ማምረት ይችላሉ።

​ለንግድ ዓላማ የሚሰማሩ በሽርክና ወይም በማህበር መደራጀት አለባቸው።

​ሕገ-ወጥ ድርጊት ሲፈጸም ወይም ግዴታን ሲያጓድሉ ፈቃድ ይሰረዛል።

​ለበለጠ መረጃ እና ዝርዝር መመሪያው ለማግኘት የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣንን ያነጋግሩ።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment