👉የኢትዮጵያ ጠቅላላ የመንገድ ርዝመት ከ180 ሺህ ኪ.ሜ በላይ ደርሷል

💫በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በጅግጅጋ ከተማ ከነሐሴ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 2ኛው ሀገር አቀፍ የመንገድ ዘርፍ ጉባኤ ተጠናቋል፡፡

🚧በመድረኩ የውይይት መነሻ ሰነዶች ዋነኛው የ2017 በጀት ዓመት የፌደራል መንገድ ዕቅድ አፈጻጸም ይገኝበታል።

⏺በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ቀ2017 ዓ.ም ከ101 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የ1,048 ኪ.ሜ የአዳዲስ መንገዶች ግንባታ፣ የነባር መንገዶች ማጠናከር፣ ደረጃ ማሻሻል እና የከባድ ጥገና እንዲሁም የ10,926 ኪ.ሜ ወቅታዊ እና መደበኛ ጥገና ማካሄድ መቻሉ ተገልጿል፡፡ የጀት ዓመቱ የፊዚካል እቅድ አፈጻጸምም 81 በመቶ ማሳካት መቻሉን የቀረበው የዘርፉ ሪፓርት ያሳያል።

⏺በተጨማሪም በሀገሪቱ ያለው ጠቅላላ የመንገድ ርዝመት በፌዴራል፣ በክልል፣ በከተሞች እና በወረዳዎች የተሰሩ ክረምት ከበጋ የሚያስኬዱ መንገዶችን ጨምሮ አምና ከነበረበት 171,176 ኪሜ አሁን ላይ 180, 232 ሺ ኪ.ሜ መድረሱ ተገልጿል፡፡

🏷ከዚህ ውስጥ 30,824 ኪ.ሜ የፌደራል፣ 36,395 ኪ.ሜ የክልል፣ 44,717 ኪ.ሜ የከተማ እንዲሁም 68,297 ኪ.ሜ የወረዳ መንገድ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

⏺ይህን ተከትሎም በ1000 ስኩዌር ኪ.ሜ ውስጥ ያለው የመንገድ ርዝመት 157 ኪ.ሜ የደረሰ ሲሆን ክረምት ከበጋ የሚያገለግል መንገድ ላይ ለመድረስ ዜጎች በአማካይ እንዲጓዙ የሚጠበቀው ርቀት 4.3 ኪ.ሜ መድረሱ ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment