👉ለዚህ ጥያቄ ብዙዎቻቺሁ 50mm ብላቺሁ ነው መልስ የሰጣቺሁ እስኪ አብረን እንየው በ EBCS EN 1992-1-1:2013 መሰረት የፋውንዴሽን ከቨር በአፈሩ ወለል ዝግጅት ላይ ተመስርቶ በሁለት ይከፍላል (Section 4.4.1.3(4) ይመልከቱ)፦

1.lean ኮንክሪት (Blinding/Lean Concrete) ከተሞላ፦ ኮዱ እንደ "Prepared ground" (የተዘጋጀ መሬት) ይቆጥረዋል። ለዚህ ሁኔታ ኖሚናል ከቨሩ ቢያንስ k_1=40ሚ.ሜ መሆን አለበት ይላል።

2. Lean ኮንክሪት (Blinding/Lean Concrete) ሳይሞላ (Cast directly against soil)፦ ኮንክሪቱ በቀጥታ በአፈር ላይ (unprepared soil) የሚሞላ ከሆነ፣ ወለሉ ወጣ ገባ ስለሚሆን ስህተት (deviation) የመፈጠር እድሉ ከፍተኛ ነው።

ስለዚህ ኖሚናል ከቨሩ ቢያንስ k_2 =75ሚ.ሜ መሆን አለበት ይላል።

ለምን የ 75 ሚ.ሜ ኖሚናል ከቨር (Nominal Cover) አስፈለገ?
የኮዱ አንቀጽ (Section 4.4.1.3(2)) የኖሚናል ከቨርን ትርጉም ሲያብራራ፡ ኖሚናል ከቨር (C_(nom)) የሚባለው በድሮይንግ ላይ የምንጽፈው ሙሉ ከቨር ነው።

ይኸውም C_(nom)= C_(min)+ ∆C_(dev) (ዝቅተኛው ከቨር + በሳይት ስራ ሊፈጠር የሚችል የስህተት ልዩነት/Deviation) ድምር ነው።

Lean ኮንክሪት (Blinding) ሳይኖር 75 ሚ.ሜ ኖሚናል ከቨር የሚያስፈልግበት ዋናው ቴክኒካዊ ምክንያት በኮዱ አንቀጽ (Section 4.4.1.3(4)) ላይ እንደሚከተለው ተብራርቷል፦

"ኮንክሪቱ ወጣ ገባ በሆኑ ወለሎች (uneven surfaces) ላይ የሚሞላ ከሆነ፣ ለሚፈጠሩ ትላልቅ ስህተቶች (deviations) እድል ለመስጠት የኖሚናል ከቨር መጠን በአጠቃላይ መጨመር አለበት።"

🚥ይህንን ወደ ሳይት እውነታ ስንቀይረው፦

1⃣. የወለል ወጣ ገባነት፦አፈር በቀጥታ ሲቆፈር ወጣ ገባ ነው፤ ወጥ የሆነ 50 ሚ.ሜ ወይም 75 ሚ.ሜ ቀጥታ ልኬት ማግኘት አስቸጋሪ ነው።
2⃣. የብረቱ ክብደትና የመሰመጥ አደጋ፦lean ኮንክሪት (Blinding) የሌለው አፈር ከባዱ የፋውንዴሽን ብረት በእሱ ላይ ሲያርፍ ወይም ኮንክሪት ሲሞላ ሰራተኞች በእሱ ላይ ሲራመዱ፣ ብረቱን የደገፉት ስፔሰሮች ክብደቱን መቋቋም አቅቷቸው አፈሩ ውስጥ ይሰምጣሉ።

🌟ስለዚህ ለተጠየቀው ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ D. 75ሚ.ሜ ነው።

​💡 ተመሳሳይ የሳይት ኢንጂነሪንግ መረጃዎችን ለማግኘት የፌስቡክ ገፃችን Follow ያድርጉ👇

https://www.facebook.com/profile.php?id=61592085774934

@​etconp

Comments

Be the first to add a comment