👉በአንድ የግንባታ ፕሮጀክት /Setting Out/በጣም ወሳኝና የመጀመሪያ ስራ ነው
━━━━━━━━━━━━━━
🗂በዚህ ደረጃ የሚደረግ ትንሽ ስህተት በኋላ ኮሎኖች፣ ግድግዳዎች፣ ቢሞች እና ጣሪያዎች ላይ ትልቅ ችግር ሊያመጣ ይችላል።
🌟1. ከሴቲንግ አውት በፊት የሚደረጉ ዝግጅቶች
✤የApproved Site Plan እና Structural Drawing በትክክል ማጥናት።
✤የመሬት ወሰን (Boundary) በሕጋዊ ሰነድ ማረጋገጥ።
✤የBenchmark (BM) መፈለግ ወይም መመስረት።
✤የGrid Line እና Column Center መጠኖችን ማረጋገጥ።
✤መሳሪያዎች (Total Station፣ Theodolite፣ Auto Level፣ Tape) ካሊብሬት መሆናቸውን ማረጋገጥ።
🌟2. ሴቲንግ አውት ሲደረግ የሚወሰዱ ጥንቃቄዎች
✤የGrid Line ርቀቶችን ሁለት ጊዜ መለካት።
✤የColumn Center ቦታዎችን ከድሮዊንግ ጋር ማነጻጸር።
✤የ90° ማዕዘን ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ።
✤ዲያጎናል (Diagonal) መለካት፤ ሁለቱ ዲያጎናሎች እኩል ከሆኑ ሌይአውቱ ትክክል ነው።
✤የLevel ልዩነትን በAuto Level መመርመር።
✤የOffset Peg እና Profile Board (Batter Board) ከቁፋሮ ውጭ ማስቀመጥ እንዳይነኩ።
✤ሁሉንም መለኪያ ከመቆፈር በፊት በኮንሰልታንት ወይም በሳይት ኢንጂነር ማረጋገጥ።
🌟3. የሴቲንግ አውት ዘዴዎች
✤Total Station – በጣም ትክክለኛ እና ዘመናዊ ዘዴ፤ ለአብዛኛው ፕሮጀክት ይመከራል።
✤Theodolite + Tape – አንግልና ርቀት በመለካት የሚሰራ።
✤Tape Measure (3-4-5 Method) – ለትንንሽ ሕንፃዎች ቀላል ዘዴ። 3m፣ 4m እና 5m በመጠቀም 90° ይፈጥራል።
✤GPS – ለትልልቅ የመሬት ፕሮጀክቶች የመጀመሪያ ኮኦርዲኔት ለማስቀመጥ ይጠቅማል።
🌟4. ምርጥ አሰራር (Best Practice)
✤አንድ ጊዜ ብቻ አትለኩ፤ "Measure twice, set out once."
✤ከቁፋሮ በፊት ኮሎን ሴንተሮችን፣ Grid Lines እና Levels በድጋሚ ያረጋግጡ።
✤የSetting Out መዝገብ (Field Book) ይያዙ፣ ሁሉንም መለኪያ ይመዝግቡ።
✤የሴቲንግ አውት ስራ በትክክል ከተሰራ፣ ፋውንዴሽን፣ ኮሎኖች፣ ቢሞች እና ሙሉ ሕንፃው በዲዛይኑ መሠረት ይገነባሉ።
@etconp