👉እናስተዋዉቃችሁ

​🌟 ቅዳሜን ከታላላቅ መሐንዲሶች ጋር፦
“ኒኮላ ቴስላ” የብርሃኑ እና የገመድ-አልባው ዓለም ጠቢብ
​
🪧ለዛሬው የቅዳሜ “እናስተዋውቃችሁ” ዓምዳችን፣ በአሁኑ ዘመን ለምንኖርበት ዘመናዊ የኢንጂነሪንግ እና የኤሌክትሪክ ስልጣኔ መሠረት የጣለውን፣ ነገር ግን በታሪክ ብዙም ሳይዘመርለት ያለፈውን ታላቅ ሳይንቲስት እና መሐንዲስ ኒኮላ ቴስላን (Nikola Tesla) ልናስተዋውቃችሁ ወደድን።

🔖​የቴስላን ሕይወት፣ ፈጠራዎች እና አስገራሚ ሚስጥሮች በአጫጭር ክፍሎች ከፋፍለን እንደሚከተለው አቅርበነዋል፦

​📌 ክፍል 1፦ ትውልድ፣ እድገት እና ያ አስፈሪ የልጅነት ትምህርት

• ​ልደቱ፦ ቴስላ የተወለደው እ.ኤ.አ. ጁላይ 10 ቀን 1856 በሰርቢያዊያን ቤተሰቦች ውስጥ (በአሁኗ ክሮኤሺያ) ስሚልጃን በተባለች መንደር ነው። በሚገርም ሁኔታ የተወለደው እጅግ ኃይለኛ የነጎድጓድና የመብረቅ ማዕበል በነበረበት እኩለ ሌሊት ላይ ነበር። አዋላጇ እናቱ “ይህ ልጅ የጨለማ ልጅ ይሆናል” ስትል፣ እናቱ ግን “አይደለም፣ የብርሃን ልጅ ነው የሚሆነው!” ብላ ተነበየችለት።
• ​ትምህርቱ፦ ቴስላ የሚገርም የማስታወስ እና የማሰብ ችሎታ (Photographic Memory) ነበረው። በኦስትሪያ ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ የኢንጂነሪንግ ትምህርቱን ሲከታተል፣ ውስብስብ የሂሳብ ቀመሮችን (Calculus) ያለምንም ስክሪፕት በጭንቅላቱ ብቻ ሰርቶ ይጨርስ ስለነበር መምህራኑ ያጭበረብራል ብለው ይጠረጥሩት ነበር። በቀን 2 ሰዓት ብቻ በመተኛት ትምህርቱን በጥልቀት ያጠና ነበር።

​📌  ዝንባሌ፣ ፈጠራዎቹ እና “የነዳጅ ፍሰት ጦርነት”
• ​መቼ፣ የት፣ ምን ፈጠረ? ቴስላ በ1884 ወደ አሜሪካ ተሰደደ። በወቅቱ ዝነኛው ቶማስ ኤዲሰን የዲሲ (Direct Current) ኤሌክትሪክን ይዞ ገበያውን ተቆጣጥሮት ነበር። ነገር ግን የኤዲሰን ዲሲ ኤሌክትሪክ ከአንድ ማይል በላይ መጓዝ አይችልም ነበር።
• ​የ-AC ሲስተም እመርታ (1887-1888፣ አሜሪካ)፦ ቴስላ ተለዋዋጭ የኤሌክትሪክ ፍሰት (Alternating Current - AC) እና ኢንደክሽን ሞተርን ፈጠረ። ይህ ሲስተም ኤሌክትሪክን በከፍተኛ ቮልቴጅ በሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎሜትሮችን በደህንነት ማጓዝ የሚችል ነበር። ይህ ፈጠራው ዛሬ መላው ዓለም፣ ፋብሪካዎችና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዎች ለሚጠቀሙበት የኤሌክትሪክ ኃይል ዋናው መሠረት ነው።
• ​የቴስላ ኮይል (1891)፦ በገመድ አልባ መንገድ ኤሌክትሪክን ለማስተላለፍ የፈጠረው ማሽን ሲሆን፣ ለዘመናዊው ሬዲዮ፣ ኤክስሬይ (X-Ray) እና የርቀት መቆጣጠሪያ (Remote Control) መፈጠር በሩን ከፍቷል።

ይቀጥላል ...

🪧YouTube ቻናላችን Subscribe ያርጉ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7

@etconp

Comments

Be the first to add a comment