የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
ሰላም!
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማደራጀት፤ ስልጣንና ተግባራቸውን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 64/2011 አንቀጽ 18 መሠረት የዐቃቤ ሕግ ቢሮ ያለው ሥልጣንና ተግባራት እንደሚከተለው ሰፍሯል፡-
1. በሕግ ጉዳዮች የከተማው አስተዳደር ዋና አማካሪና ተወካይ ሆኖ ይሠራል፤
2. የከተማውን የፍትህ ሥርዓት ማሻሻያ ፕሮግራምን ያቅዳል፤ ያስተባብራል፤ በእቅድ መሰረት መከናወኑን ያረጋግጣል፤ ይከታተላል፤ ክፍተቶችን እየለየ ድጋፍ ያደርጋል፤
3. የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሀ ግብር ይተገብራል፤ አስፈፃሚ አካላት በዋና ዕቅዳቸው ማካተታቸውን ያረጋግጣል፤ ይደግፋል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤ ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት ያቀርባል፤
4. ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል ፕሮግራሞችን ይቀርፃል፤ በሚመለከተው አካል ሲጸድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤ ይመራል፤ ያስተባብራል፤ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፤
5. የከተማው አስተዳደር መስሪያ ቤቶች የአስተዳደሩና የነዋሪው መብትና ጥቅም ወኪል ሆኖ ይከራከራል፣ ያስከብራል፣ የሚከበሩበትን ሂደት ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
6. የከተማው አስተዳደር የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚያደርጉትን ውል እንደአስፈላጊነቱ ይመረምራል፤ ሕጋዊነታቸውን ያረጋግጣል፤ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፤ ተገቢው የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል ወይም ይወስዳል፤
7. የከተማው አስተዳደር የመንግስት መስሪያ ቤትን እና የመንግስት ልማት ድርጅቶችን በመወከል በማንኛውም የዳኝነት ሥልጣን በተሰጠው አካል ወይም በግልግል ጉባኤ በመቅረብ ክስ ይመሰርታል፣ መልስ ይሰጣል፣ የጣልቃ ገብ፣ የመቃወም እና የይግባኝ አቤቱታ ያቀርባል፤
8. የከተማ አስተዳደሩን የህዝብ መብትና ጥቅም ለማስከበር አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በማንኛውም የዳኝነት ሥልጣን በተሰጠው አካል ወይም በግልግል ጉባኤ በመቅረብ በስሙ ክስ ይመሠረታል፤ መልስ ይሰጣል፤ የጣልቃ ገብ አቤቱታ ያቀርባል፤ ይግባኝ ይጠይቃል፤
9. የተሰጠው ውሣኔ የህዝብንና የመንግስትን ጥቅም የሚጏዳ ሆኖ ካገኘው የመቃወም አቤቱታ ያቀርባል፤ ይከራከራል፤
10. የአስተዳደሩ ተቋማት ከአሰሪና ሰራተኛ ጋር ተያይዘው የሚቀርቡ የክርክር ጉዳዮችን ወክሎ ይከራከራል፤ ያስወስናል፤ ያስፈጽማል፤
11. በከተማው አስተዳደር የመንግስት መስሪያ ቤቶች እርስ በእርሳቸው ያልተግባቡባቸው የፍትሐብሔር ጉዳዮች በፍርድ ቤት ወይም ከፍርድ ቤት ውጪ ባለ አማራጭ የክርክር መፍቻ መንገድ እንዲወሰን ውሣኔ ይሰጣል፣ በውሣኔ መሠረት መፈፀሙን ይከታተላል፤
12. በካቢኔው በሚፀድቅ ወይም በፀደቀ መዋቅራዊ አደረጃጀት መሠረት የራሳቸው የሕግ አገልግሎት እንዲኖራቸው የተፈቀደላቸው አካላትን የህግ አገልግሎቶች በሚመለከት ወቅታዊ ሪፖርት እንዲቀርብለት ያደርጋል፤ የጉዳይ አያያዛቸውን ወይም ስራቸውን ይከታተላል፤ ይደግፋል፤ ይቆጣጠራል፤ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፤
13. በሌሎች ሕጏች የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ በፍርድ ቤት የተያዘ ወይም ፈርድ ቤት ከመቅረባቸው በፊት የማያዋጡ ወይም ለአላስፈላጊ ወጪ የሚዲርጉ ጉዳዮችን በአማራጭ ክርክር መፍቻ ዘዴዎች እንዲፈቱ ያደርጋል፤
14. በከተማው ውስጥ ለሚኖሩ አቅም ለሌላቸው ነዋሪዎች ነፃ የህግ ምክር ድጋፍ ይሰጣል፤
15. በዐቃቢያነ ሕግ የሚሰጡ ውሣኔዎች በሕግ መሠረት መከናወናቸውን ያረጋግጣል፤ ጉድለቶችን በጥናት አስደግፎ ይለያል፤ በግኝቱ መሠረትም እንዲታረሙ ያደርጋል፤ አስፈላጊ ሲሆን እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰው ያደርጋል፤
16. የሕግ ጥናትና ምርምር ያደርጋል፤ የከተማው አስተዳደር ያወጣቸው ሕጎች በአግባቡ ስራ ሊይ መዋላቸውን ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤ ይጠብቃል፤ የሕግ ወይም የውሌ ረቂቅ ያዘጋጃል፤
17. ነዋሪው በሕገ መንግስቱና በቻርተሩ የተሰጡትን መብቶችና ነጻነቶች እንዲያውቅና እንዲጠቀም ተገቢውን የሕግ ስልጠና ይሰጣል፤
18. ለከተማው አስፈጻሚ አካላትና የልማት ድርጅቶች አመራሮችና ሰራተኞች የንቃተ ሕግ ስልጠና ይሰጣል፤
19. አግባብ ባለው ሕግ መሰረት በከተማው ፍርድ ቤት ሥልጣን ስር የሚወድቁ የወንጀል ጉዳዮችን በተመለከተ ክስ ይመሰርታል፤ ይከራከራል፤ አግባብነት ያላቸውን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፤
20. ከፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ፣ ከሚመለከተው አካል ወይም በህግ በውክልና የሚሰጡትን የወንጀል ጉዳዮች ይከራከራል፤ያስወስናል፤ ያስፈጽማል፤
21. በሕግ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የደንብ መተላለፍ ጉዳዮችን በከተማው ፖሊስ ተጣርቶ ሲቀርብለት ወይም እንዲቀርብለት በማድረግ ክስ ይመሰርታል፣ ይከራከራል፤ የተጀመረ ምርመራ በሕግ መሠረት እንዲቆም ያዛል፤ ክስ ያነሣል ወይም የምርመራ መዝገቡ በሕጉ መሠረት ይዘጋል፤ ሌሎች ሕጋዊ ተግባራትን ያከናውናል፤
22. በከተማው አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት የሚጣሉ የደንብ መተላለፍ ቅጣቶችን ያስፈፅማል፤ ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፤
23. በካቢኔ የጸደቀ ደንብ በአዲስ ነጋሪ ጋዜጣ ያሳትማል፤ የከተማው ሕጎችን መሰብሰብ ማደራጀት መተንተንና ማሰራጨት የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል፤ ይፈጽማል፤
24. የከተማው አስተዳደር የሚሰጣቸው አስተዳደራዊ ውሣኔዎች ከሕግ ጋር የተጣጣመ መሆኑን ያረጋግጣል፤ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲወሰድ ያደርጋል፤ ምክር ይሰጣል::
ቸር ያሰማን! (17/07/2013 ዓ.ም) (ኦምኒኤል)
Comments
Be the first to add a comment