የምህንድስና ተአምር!
በግንባታውና በመሠረተ-ልማቱ ዓለም የቻይናን የምህንድስና ጥበብና ፍጥነት የሚስተካከል ያለ አይመስልም፤
በቅርቡ የወጣ ዓለም አቀፍ ዜና እንደሚያሳየው፣ ቻይና በምህንድስናው ዘርፍ ሌላ አዲስ የዓለም ክብረ-ወሰን አስመዝግባለች፤
በደቡብ ምዕራብ ቻይና በምትገኘውና በተራራማ መልክዓ-ምድሯ በሚታወቀው ጉይዥው ግዛት ላይ እየተገነባ ያለው Nanpanjiang Bridge፣ በዓለማችን ረጅሙ የቅስት ድልድይ (World's largest span half-through arch bridge) የመሆን ታሪካዊ ምዕራፍን በትላንትናው ዕለት አሳክቷል፤
ለሁለት የተከፈሉት ግዙፍ የብረት ቅስቶች በከፍተኛ ጥንቃቄ ተንቀሳቅሰው በሰማይ ላይ ልክ እንደ ቀስተ-ደመና በትክክል እርስ በርስ የተገጣጠሙበት ቅጽበት መላውን የምህንድስና ዓለም ጉድ አሰኝቷል፤
ይህ ድልድይ ተራ ግንባታ አይደለም፤ የተፈጥሮን አስቸጋሪ መልክዓ-ምድር በሰው ልጅ ዕውቀት የማሸነፍ ጥበብ እንጂ!
የድልድዩ ዋናው ቅስት ብቻውን 416 ሜትር ርዝማኔ ያለው ሲሆን፣ አጠቃላይ የድልድዩ ርዝመት ደግሞ 915 ሜትር ይደርሳል፤
ይህንን ግዙፍ ድልድይ በተራራማና ጥልቅ ሸለቆ ባለበት አስቸጋሪ ቦታ ላይ፣ ያውም በከፍተኛ ንፋስና የአየር ንብረት ተጽዕኖ ውስጥ ሆኖ ሚሊሜትር ሳይሳቱ በሰማይ ላይ በትክክል ማገናኘት እጅግ አስገራሚ የምህንድስና ብቃት የሚጠይቅ ነው፤
ግንባታው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ፣ በአካባቢው ያለውን የትራንስፖርት ትስስር ፍጹም በማቀላጠፍ ለቀጣናው የኢኮኖሚ ዕድገት አዲስ የጀርባ አጥንት እንደሚሆን ይጠበቃል፤
ይህንን ታላቅ ፕሮጀክት ስንመለከት፣ መሠረተ-ልማትና ከባድ ማሽነሪዎች የአንድን አገር የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንዴት እንደሚቀይሩ በተጨባጭ እንረዳለን።
@etconp