🏠 100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያለው የቤት መግዣ ፋይናንስ ተቋም ሊቋቋም መሆኑን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳወቁ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስን ለማስፋፋት የትብብር ማዕቀፍ ተፈራርመዋል።

በ100 ቢሊዮንብር ካፒታል የሚቋቋመው ተቋም IFC እስከ 200 ሚሊዮን ዶላር አስተዋጽኦ ያደርግበታል።

ተቋሙ የቤት መግዣ ብድርን በመላ አገሪቱ ለማስፋፋትና የ1.5 ሚሊዮን ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው ቤቶችን ለመገንባት የተቀመጠውን ግብን ለማሳካት ያግዛል ሲሉ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment