3.የማይስተባበል የሕሊና ግምት (irrebuttable/ conclusive presumption)
-የሚባለዉ ምንም ዓይነት የማስተባበያ ተቃራኒ ማስረጃ ቢቀርብ እንኳ፤ መነሻ የሆነዉ መሠረታዊ ፍሬ ነገር በማስረጃ ከተረጋገጠ ፍ/ቤት አከራካሪ ሆኖ የተገኘዉ ፍሬ ነገር መኖርና አለመኖሩን እንደሚስረዳ አምኖ መቀበል እንዳለበት በሕግ የታዘዘዉ የሚጸና ሲሆን ነዉ፡፡
ለምሳሌ፡- የፍ/ብ/ሕ/ቁ 3(1)
አንድ ልጅ ከተወለደበት ጊዜ አንስቶ 300 ቀን (10 ወር) በፊት እንደተጸነሰ ይቆጠራል ሲል
(2) ይህንንም ግምት መቃወሚያ የሚሆን ማንኛዉንም ማስረጃ ማቅረብ አንደማይቻል ይደነግጋል
-እንግዲህ ልጁ የተጸነሰበትን ቀን ፍ/ቤቱ የሕሊና ግምት እንዲወስድበት የሚጠይቅ ወገን በማስረጃ ማረጋገጥ ያለበት መሠረታዊ ፍሬ ነገር ልጁ በሕይወት መወለዱን ብቻ ነዉ፡፡ ስለዚህ ልጁ የተወለደዉ ከተወለደ ከ300 ቀን ባነሰ ጊዜ ዉስጥ ነዉ የተጸነሰዉ ብሎ ተቃራኒ ማስረጃ ማቅረብ አይቻልም፡፡
ሕድአት ጌታቸዉ
የካቲት/2014 ዓ.ም

Comments

Be the first to add a comment