🌴 *
فَضلُ يَومِ عَرَفَةَ والعَمَل فيهِ* 🌴♻️*
የዐረፋ ቀን ትሩፋት እና በሱ ላይ የተደነገጉ ተግባራት*🌱 قَالَ رَسولُ اللهِ
🤩 :
*صِيَامُ يَوْمِ عَرَفَةَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ، وَالسَّنَةَ الَّتِي بَعْدَهُ*
📚 رواهُ مُسلِم (1162)
የአላህ መልዕክተኛ
🤩 እንዲህ ብለዋል «የዐረፋ እለት ፆም… ከዚህ አመት ቀድሞ ያለውንና የቀጣዩን ኣመት እንደሚያስምርልን ከአላህ ኣስባለሁ።»
【ሰሂሁ-ሙስሊም: 1162】
ይህንን በማስመልከት ሸይኽ ሷሊህ አልዑሰይሚን [ረሂመሁላህ] “የዐረፋ እለት ፆም ያለፈው አመትንና የቀጣዩ አመትን ያስምራል። ሲባል ጥቃቅን ሀጢኣቶችን ብቻ የሚመለከት ነው። ከባባዶቹ ወንጀሎችን በተመለከተ የግድ ንስሃ መግባት ተውበት ማድረግ ይገባል።” ብለዋል።
【ፈታዋ ኑ…ሩን አለ-ድ'ደርብ: የካሴት ቁጥር ☞328】
በመሆኑም በዚሁ አጋጣሚ ከሐጢኣቶቻችን በመፀፀት ወደ ጌታችን በመመለስ ተውበት ከማድረግ ጋር የነገዋን የአረፋ እለት በፆም እናሳልፍ። የሰው ልጆች ነንና ከወንጀል ስለማንፀዳ ወንጀሎቻችንን እናራግፍ።
🔵የዐረፋ እለት ዱዓእ ከሌላው ቀን የተሻለ የሆነ ዱዓእ ነውና እጆቻችንን እናንሳ።
🌱 قَالَ رَسولُ اللهِ
🤩 :
*خَيْرُ الدُّعَاءِ دُعَاءُ يَوْمِ عَرَفَةَ، وَخَيْرُ مَا قُلْتُ أَنَا وَالنَّبِيُّونَ مِنْ قَبْلِي: لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ*
📚 صحيحُ الجامع (3274)
የአላህ መልዕክተኛ
🤩 እንዲህ ብለዋል፦ «ከዱዓኦች በላጩ የዐረፋ እለት ዱዓእ ነው። እኔም ሆንኩ ከኔ በስተፊት የነበሩት ነቢያት ከተናገሩት መካከል በላጩ ቃል "ከአላህ በስተቀር በሀቅ ሊመለክ የሚገባው አምላክ የለም… እሱም ብቸኛና አጋር የሌለው ነው … ንግስናም ምስጋናም ለሱ የተገባ ነው … እሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ የሆነ ነውና።" የሚለው ቃል ነው።»
【ሰሂሁ-ቲርሚዚይ: 3585, አል-አልባኒም ሀሰን ብለውታል】
ሸይኽ ዶክተር ሷሊህ ፈውዛን አል-ፈውዛን [ሀፊዘሁላህ] ስለዚህ ዱዓእ ሲያስረዱን☞
«የዐረፋ እለት ዱዓእ ሐጃጆችንም ሀጅ የማያደርጉትንም የሚያጠቃልል ነው። የሀጃጆች ግን ለየት ይላል። ምክንያቱም እነሱ ብልጫ ባለው ስፍራ ኢህራም ለብሰው በዐረፋ ምድር ቆመዋልና።» ብለዋል።
ከድምፃቸው በቀጣዩ ሊንክ ያድምጡ⇣
⬇️http://www.alfawzan.af.org.sa/sites/default/files/240.mp3 🔵የዐረፋ እለት ከእሳት ነፃ የሚኮንበት ቀን ነው። በእለቱም በዐረፋ ምድር ለተገኙት ሀጃጆች ብቻ ሳይሆን ለመላው ሙስሊም ከእሳት ነፃ መውጫ ነውና ከወዲሁ በተውበትና በዒባዳ ነቃ እንበል።
🌱 قَالَ رَسولُ اللهِ
🤩 :
*مَا مِنْ يَوْمٍ أَكْثَرَ مِنْ أَنْ يُعْتِقَ اللهُ فِيهِ عَبْدًا مِنَ النَّارِ مِنْ يَوْمِ عَرَفَةَ، وَإِنَّهُ لَيَدْنُو، ثُمَّ يُبَاهِي بِهِمُ الْمَلَائِكَةَ، فَيَقُولُ: مَا أَرَادَ هَؤُلَاءِ*
📚 رواهُ مُسلِم (1348)
የአላህ መልዕክተኛ
🤩 እንዲህ ብለዋል «አላህ ከባሮቹ መካከል በብዛት ከእሳት ነፃ ከሚያደርግባቸው እለታት ከዐረፋ እለት የበለጠ የለም። አላህም በእለቱ ወደነሱ ይቀርባል። መላኢኮቹንም እነዚያ ሰዎች ምን ፈለጉ ይላቸዋል።»
[ሰሂሁ-ሙስሊም: 1348]
ልእለ ሀያሉ ጌታችን የያንዳንዳችንን ፍላጎትና አላማ እያወቀ ለመላእክት ጥያቄ ማቅረቡም በእለቱ የሚለምኑትን ባሮቹን ለመላእክቶች ለማሳወቅና ለማስመስከር ነው።
⭐️ ሃፊዝ ኢብኑ ሀጀር [ረሂመሁላህ]
«የዐረፋ ቀን ከእሳት ነፃ የሚወጣበት ቀን ነው። አላህ (በሀጅ ተግባር) በዐረፋ ምድር የቆመን ሰው ከእሳት ነፃ ይለዋል። በዐረፋ ምድር ያልተገኘን በተለያዩ ሀገራት የሚገኙትንም ሙስሊሞች በእለቱ ከእሳት ነፃ ያደርጋቸዋል። ለዚህም ሲባል ነው ከዐረፋ እለት ቀጥሎ ያለውን ቀን በሀጅ ላይ ለተሳተፉትም ላልተሳተፉትም በያሉበት ሀገሮቻቸው ለመላው ሙስሊሞች የዒድ ቀን ያደረገው። ይህም ከእሳት ነፃ በመውጣቱና ከአላህ ምህረትንም በማግኘቱ ረገድ ሁሉም ስለሚጋሩ ነው።» ብለዋል።
[ ለጧኢፉል-መዓሪፍ… ሊኢብኒ-ረጀብ አል-ሀንበሊይ]
---------
وَفَّقني اللهُ وإيَّاكم لما يُحبُّ ويرضى
وجعلنا من عتقاء اللهِ في هذا اليوم المبارك، ونسألُ اللهَ من فَضلهِ الوَاسع
〰〰 〰〰 〰〰 〰〰 〰〰🎴📎😊 ᵗᵉʷʰᵉᵈᵃⁿᵈˢᵘⁿᵃ👈🟢📣
🤩