✿ ክብሩን ሲያጣ...

ፈረስ ለግልቢያና ለውብ ኮርቻ አልበጅም ሲል ልክ እንደ አህያ እቃ መጫኛ ይሆናል፤
ላምና በሬም ለርቢና ለእርሻ አልበጅም ሲሉ ለቢላዋ ይዳረጋሉ፤
ቢላዋም ስጋ አልቆርጥም ሲል እንጨት መሰንጠቂያ ይደረጋል፤ ወዘተ... ማንኛውም ለተሰራለት ዓላማ የማይውል ነገር ክብርና ደረጃውን ያጣል።

አንተም/ቺም ለመልካም ሥራና ለጀነት አልበጅም ካልክ/ሽ (አላህን سبحانہ وتعالى ካልታዘዝን) ጀነትን ተነፍገን ለጀሀነም እሳት መዳረግ አይቀርምና ጠንቀቅ እንበል!

በሁለቱም ዓለም ውድና ክቡር እንድንሆን ለተፈጠርንለት ዓላማ እንኑር።

© ahmedadem

🌱 @TewhedandSuna

Comments

Be the first to add a comment