አንድ ፍርድ እንደገና እንዲታይ በመጀመሪያ ፍርዱን በሰጠዉ ፍ/ቤት እንደገና ስለሚታይበት ሁኔታ
1. የስነ-ስርዓት ጉድለት
2. አዲስ መስረጃ ማግኘት
3. መቃወሚያ
የስነ-ስርዓት ጉድለት
ፍርዱን የሰጠዉ ፍ/ቤት የሕጉን ድንጋጌዎች ባለመከተሉ የሥነ-ሥርዓት ጉድለት የፈጸመ እደሆነና ይህም ጉድለት አንዱን ተከራካሪ ወገን በሚጎዳ ሁኔታ የጉዳዩን ዉሣኔ አሰጣጥ በእጅጉ ያዛባዉ እንደሆነ ፍርዱን ሊያነሣዉ ይችላል፡፡
የሥነ-ስርዓት ጉድለቱ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ከመቅረቡ በፊት ወይም በዚሁ የክርክር ሂደት የተፈጸመ እንደሆነ በሥነ-ሥርዓቱ ጉለት ምክንያት በደል ደረሰብኝ የሚለዉ ተከራካሪ ተቃዉሞዉን በዚያዉ ጊዜ ማቅረብ አለበት፡፡
ጉድለቱ የተፈጸመዉ የሥነ-ሥርዓት ደንቦችን ባለመከተል የሆነ እንደሆነ ፍ/ቤቱ በራሱ ወይም በአንዱ ተከራካሪ ጠያቂነት የክርክሩን ሂደት በሙሉ ወይም በከፊል በጉድለቱ ምክንያት ሊሰርዘዉ ሊያሻሽለዉ ወይም ተገቢ መስሎ የታየዉን ሌላ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል፡፡
ፍ/ቤቱ በተሰጠዉ መጥሪያ በወሰነዉ ፍርድ በሰጠዉ ዉሣኔና ትዕዛዝ ላይ የአጻጻፍ ሥህተት፤ የቁጥር አጻጻፍ ጉድለት ወይም ያልታሰበና ባለማስተዋል የተዘለለ ድንገተኛ የቃል ሥህተት መኖሩን ያረጋገጠ እንደሆነ ወይም ከባለጉዳዮቹ አንዱ ሲያመለክት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 107 የተነገረዉን የስነ ሥርዓት ጉድለት ካልሆነ በቀር ፍ/ቤቱ ሊያርመዉ ይችላል፡፡
የተሰጠዉን ዉሣኔ በመሠረታዊነት ሊለዉጥ የሚችል ወይም በተከራካሪ ወገን ላይ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ከሆነ ፍ/ቤቱ የክርክሩን ሂደት መሰረዝ ቀጠሮ ሰጥቶ እንደ አዲስ ክርክር እንዲካሄድ ካደረገ በኋላ ዉሣኔ ይሰጣል፡፡ ዉሣኔዉ መሰረታዊ ጉድለት የማያደርስ ከሆነና ጉድለቱ ሊታረም የሚችል ከሆነ የክርክሩ ሂደት ላይሰረዝ ይችላል፡፡
የስነ-ስርዓት ጉድለቱ እንደ ይግባን ምክንያት ሊሆን የሚችለዉ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 209 መሰረት ማመልከቻ ካልቀረበና ጉድለቱ ከተሰጠዉ ፍርድ ወይም ዉሳኔ ጋር የተያያዘ ከሆነ ነዉ፡፡
የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 209(3)፤ 207፤ 209(1)፤ 208፤ 210(1)፤ 211
ሴድለር
ህድአት ሐምሌ/2013 ዓ.ም

Comments

Be the first to add a comment