✿
የዒድ በዓል ስነ-ስርዓቶች (آداب العيد)▢
የዒድ ሰላት ስነ-ስርዓቶች (آداب صلاة العيد)•
ገላን መታጠብና ሽቶ መቀባት፦ ለዒድ ሰላት ገላን መታጠብ፣ ሽቶ መቀባትና በጥሩ/በሚያምር ሁኔታ ተውቦ መውጣት የተወደደ (ሙስተሐብ) ነው።
•
መንገድ መቀየር፦ ሰጋጁ ወደ ዒድ ሰላት በአንድ መንገድ ከሄደ፣ ሲመለስ በሌላ መንገድ መመለሱ የነቢዩ ሱና ነው።
•
ማለዳ መውጣት፦ ከፈጅር ሰላት በኋላ ወደ ዒድ ሰላት ቀድሞ መውጣትና እየተራመዱ (በእግር) መሄድ ሱና ነው።
•
የሰላት ቦታ፦ የዒድ ሰላትን በሜዳ (ክፍት ቦታ) መስገድ ሱና ነው።
•
እጅን ማንሳት፦ ለእያንዳንዱ የዒድ ሰላት ተክቢራ እጅን ወደ ላይ ማንሳት ሱና ነው።
▢
የዒድ ቀን ስነ-ስርዓቶች (آداب يوم العيد)•
እንኳን አደረሳችሁ መባባል፦ በዒድ ቀን የእንኳን አደረሳችሁ የእንኳን አደረሰህ የደስታ መግለጫ መልእክቶችን መለዋወጥ የተፈቀደ (የተደነገገ) ነው።
•
ተክቢራ ማድረግ፦ ከዙልሒጃ መጀመሪያ ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው የታሽሪቅ ቀን ጀምበር ግባት ድረስ ተክቢራ ማድረግ (አላህን ማክበር) የተደነገገ ነው።
•
ፈቀድ የተደረጉ ነገሮች፦ በዒድ ቀን በተፈቀዱ (ሀላል) በሆኑ የደስታ መግለጫዎች ላይ መሳተፍ ይፈቀዳል። ለምሳሌ፦ የልጆች ጨዋታ፣ የታናናሽ ሴት ልጆች መዝሙር/እንጉርጉሮ እና የመሳሰሉት።
@TewhedandSuna