ጤና ይስጥልኝ
በኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 40/3 ስር መሬት የመንግሥትና የሕዝብ ንብረት መሆኑንና ስለዚሁ ንብረት ባለቤትነት ተደንግጎ የምናገኘው ይህው የኢፌድሪ ሕገ-መንግስት ከመጽደቁ ከአርባ (40) ዓመታት በፊት በሐምሌ 19 ቀን 1967 ዓ.ም የወጣውና ከነሐሴ 1 ቀን 1967 ዓ.ም ጀምሮ የጸናው ባለ 46 አናቅጽቱ "የከተማን ቦታና ትርፍ ቤት የመንግሥት ንብረት ለማድረግ የወጣው አዋጅ ቁጥር 47/1967 ዓ.ም " ሲሆን በዚህ አዋጅ ላይ አሁን በየከተሞች ላይ የምናያውን "የቀበሌ ቤት" እና "የኪራይ ቤቶች " (የመንግስት ቤት ) ከዚህ በላይ በገለጽነው አዋጅ ቁጥር 47/67 በኪራይ መጠን በመነሳት የለየበትንና በማን እንዲተዳደሩ እንዳደረገ እንመልከት፡፡
መልካም ምንባብ፡-
በአዋጅ ቁጥር 47/67 ላይ ከተጠቀሱት ተቋማት በጉልህ የምናገኘው የከተማ ነዋሪዎች ኀብረት ሥራ ማህበራት (ከነማ) አንዱ ሲሆን ይህም በየደረጃው ማህበራቱን የሚያሰተባብሩ የከፍተኛ እና የአጠቃላይ የከተማ ነዋሪዎች ሥራ ማህበር የተቋቋሙና ከእነዚሁ ጋርም በከተማ ነዋሪዎች የሚነሱ የከተማ ቦታና የቤት ክርክርን የሚመለከቱ የፍርድ ሽንጎ የተቋቋሙ ሲሆን እንደዚሁም ስለአጠቃላይ የተወረሱ ቤቶችን ከበላይ ሆኖ የሚያስተባብረውን የሥራና የቤቶች ሚኒስቴር መሥሪያ ቤትን ደግሞ በአዋጁ ላይ ጠቅሶ በትርፍ ቤትነት ተከራይተው የነበሩ ቤቶች እንደየቤት ኪራይ የገንዘብ መጠን ከ50 በመቶ እስከ 15 በመቶ ቅናሽ በማድረግና በዚሁ ተቀናሽ ሂሳብ መሠረት የቤት ኪራይ መጠናቸው እስከ ብር 100 (አንድመቶ ብር) የሆኑት ቤቶች የከተማ ነዋሪዎች የኅብረት ሥራ ማህበር ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ኪራዮን ሲሰበሰቡ ከብር 100(አንድ መቶ ብር ) በላይ የሚከራዩ የመኖሪያ ቤቶች ወይም መሠሪያ ቤቶችን በኃላፊነት የሚያስተዳድረው የሚኒስቴር መ/ቤቱ እንዲሆን በማድረግ በከተሞች ውስጥ የሚገኙ ቤቶችን በማን ኪራዩ እንዲሰበሰብም ሆነ እንዲተዳደሩ እንደተደረገ ግንዛቤ ልንይዝበት እንደሚገባ በመግለጽ አበቃን ፡፡
መልካም ቀን!!!
በቃ # No More
ታህሳስ 13/2014ዓ.ም
ደረጀ ማርቆስ

Comments

Be the first to add a comment