👉ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፓሬሽን ከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት እየተገበረ ለሚገኘው መጠነ ሰፊ የቤት ልማት ፕሮግራም በግንባታው ዘርፍ ላይ የተሰማሩ እና መስፈርቱን የሚያሟሉ ስራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይጋብዛል፡፡

⏺በዚሁ መነሻ

1. ለስራ ተቋራጮች ምዝገባ መሟላት ያሉባቸው መረጃዎች፡-
 
ሀ) የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገቡ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤

ለ) በምዝገባው ወቅት የሰነዶቹን ዋና እና አንድ የማይመለስ ቅጂ በአካል የሚቀርብ ሆኖ የስራ ተቋራጩ የበላይ ኃላፊ፣ ባለቤት ወይም ህጋዊ ውክልና ያለው ተወካይ ፊርማ እና የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

2. ከደረጃ 1-4 ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ(GC) እና ( BC )ህንፃ ተቋራጭ እንዲሁም ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ (GC) ደረጃ 5 የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው በግንባታው ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ስራ ተቋራጮች ተሳታፊ መሆን ይችላሉ ።

3. ከቅዳሜ  9 /12/2018 ዓ/ም (ከጠዋቱ 2፡30) ቅዳሜ ሙሉ ቀን ጨምሮ ለ5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት( እስከ ሀሙስ 14/12/2018 ዓ/ም ከሰዓት 11፡30) በአካል በመቅረብ በኮርፖሬሽኑ 11ኛ ወለል በሚገኝ አዳራሽ ላይ ምዝገባ በማድረግ መረጃዎቹ መሟላታቸው በመዝጋቢው ሲረጋገጥ ለዚሁ የተዘጋጀ የቴክኒካል ሰነድ መግዛት ይቻላል።

4. ተገቢውን ሰነድ በማቅረብ የምዝገባ ሂደቱን በሚገባ ያሟለ ተቋራጮችን በተመለከተ ምዝገባው በተጠናቀቀ በ 24 ሰዓት ውስጥ በቀን 15/12/2018 ዓ/ም በተቋሙ ማህበራዊ ድህረ ገጽ እና በኮርፖሬሽኑ የማስታወቂያ ቦርድ 11ኛ ወለል የሚለጠፍ ይሆናል፡፡

5. ተቋራጮች የቅድመ ምዝገባ ውጤት ከታወቀበት ቀን ጀምሮ በአስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ቅጂ የቴክኒካል ፕሮፖዛላቸውን ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን እስከ ቀን 27/12/2018 ዓ/ም ከሰዓት 11:30 ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. ተቋራጮች ለምዝገባ እና ለቴክኒካል ሰነድ ግዢ የማይመለስ ብር ለደረጃ 1 ብር 7,500 (ሰባትሺ አምስት መቶ ብር ) ፣ ለደረጃ 2 ብር 6,500 ( ስድስት ሺ  አምስት መቶ ብር ) እና ለደረጃ 3 ብር 5,500 አምስት ሺ አምስት መቶ ብር ) ፣ ለደረጃ 4 ብር 5,000 (አምስት ሺ ብር ) ፣ ለደረጃ 5 ብር 4,500 አራት ሺ አምስት ብር ) መክፈል ይጠበቅባቸዋል፡፡

አድራሻ፦በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክ/ተማ ወረዳ 01
 
በተለምዶ ባምቢስ አከባቢ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ና አስተዳደር ቢሮ ህንፃ ላይ 11ኛ ወለል እንገኛለን።

ነሀሴ 9 ቀን 2018 ዓ/ም

የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

@etconp

Comments

Be the first to add a comment