ቢሮዉ ባለፉት ሁለት ሳምንታት 122 የኮንዶሚኒየም ካርታዎች ማተሙን ገለጸ

የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ፣ ባለፉት ሁለት ሳምንታት 122 የኮንዶሚኒየም ካርታዎችን በማተምም ለባለቤቶቹ እንዲደርሱ ማድረጉን ይፋ አድርጓል።

ቢሮዉ የ90 ቀናት ዕቅድ በማዘጋጀትና አፈፃፀሙን በገመገመበት ወቅት፣ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከ4 ሺህ 5መቶ በላይ አገልግሎቶችን በስታንዳርድ መሠረት መስጠት መቻሉንም ገልጿል፡፡

በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ 744 የቀበሌ ቤቶች መብት መፍጠር ስለመቻሉም አረጋግጧል፡፡

ከዚህም በተጓዳኝ በክርክር መዝገብ ውስጥ ገብተው ነበሩ ያላቸዉን 564 ማህደራት ተለይተው ማስተካከያ እንዲደረግባቸው በማድረግ በዜጎች ዘንድ ይከሰት የነበረን እንግልት ማስቀረት ተችሏል ብሏል።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment