This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌙 ​የረመዳን አጋማሽ 🥹

• ​የአላህ ባሪያዎች ሆይ! እነሆ የረመዳን ወር አጋማሽ ላይ ደርሷል። ከእናንተ መካከል በዚህ ወር ውስጥ ራሱን የፈተሸና የቀና ማን አለ?

• ​በዚህ ወር የሚገባውን ክብር የሰጠውና መብቱን ያወቀ ማን አለ? እነሆ ወራችሁ መጉደል (ማለቅ) ጀምሯል፤ ስለዚህ በበጎ ስራዎች ላይ በርቱ።

• ​ወሩ ሊጠናቀቅ እንደሆነ ሁሉ፣ እያንዳንዱ ወር መጨረሻ አለው። ለሌሎች ወራት ምትክ ሊኖር ይችላል፤ ለረመዳን ግን ምትክ ከየት ይገኛል?

• ​ወሩ አጋማሽ ላይ ደርሷል ፣ መልካምን ስሩ ፤ በጀነቶችም ውስጥ ድልን የሚቀዳጁት በርትተው ያገለገሉ (የሰሩ) ናቸው።

• ​እንደ እኔ አይነቱ ዘንጊና ምስኪን ግን በሀዘን ተሰብሯል፤ ዋይ ለርሱ! ከዚህ ትልቅ እድል መታረሙ ምንኛ ከባድ ነው።

•​በመዝራት ወቅት ዘር ያመለጠው ሰው፣ ከመጸጸትና ከሀዘን ውጭ ምን ሊያጭድ ይችላል?

•​በዚህ ወር ውስጥ አላህን በመፍራት (ተቅዋ) የነገደና የአላህ ገመድ አጥብቆ የያዘ ሰው ምንኛ የታደለ ነው!

🔵 @TewhedandSuna 🌐

Comments

Be the first to add a comment