የአፈር ኪራይ የቀጠለ…..
በጂ.አይ.ኤስ እና በሲ.አይ.ኤስ የመረጃ ቋት ላይ ሁለትና ከዚያ በላይ የቤት ቁጥሮች የተገለጹ ነገር ግን በአንድ የቤት ቁጥር የአፈር ኪራይና የህንጻ ግብር ሲገብሩ የነበሩ ባለይዞታዎች ይዞታዎች መስተንግዶ አሰጣጥን በተመለከተ፡-
ደብተር ያላቸው ወይም የሌላቸው ይዞታዎች ሆነው ደብተሩ ላይ ወይም በአፈር ግብር ካርኒው ላይ አንድና ከዚያ በላይ የቤት ቁጥሮች ካላቸው፣
በጂ.አይ.ኤስና በሲ.አይ.ኤስ የመረጃ ቋት የቤት ቁጥሩ ተገልጾ የግል ይዞታ ስለመሆኑ በሲ.አይ.ኤስ መረጃ ቋት ላይ ከተገለጸ ወይም፣
ባለይዞታው የቦታ ኪራይና የህንጻ ግብር በአንድ የቤት ቁጥር የሚከፈል ቢሆንም ቤቶቹ ሌላ ሰው ወይም አካል ይገባኛል ጥያቄ የሌለባቸው መሆኑን እና ቤቶቹ አሁንም ያሉና በመስተንግዶ ጠያቂዎቹ እጅ የሚገኙ መሆናቸዉን ሲረጋገጥ እና
የወረዳው ኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ጽ/ቤት እያስተዳደራቸው ስለመሆን አለመሆኑ በደብዳቤ እንዲጠየቅ በማድረግ ቤቶቹን እያስተዳደራቸው አለመሆኑ ወይም የመንግስት/የቀበሌ ቤት መሆኑ መረጃ ያልቀረበበት መሆኑ ሲረጋገጥ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ይሰጣቸዋል፣
ከላይ በተራ ቁጥር 26.1.3 ላይ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የመረጃ ልዩነት ካለበዚህ መመሪያ ስለመረጃ እርማት በተደነገገው አግባብ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
ትራንስፎርምድ በተደረገው ጂ.አይ.ኤስ እና ትራንስፎርም ባልተደረገው ጂ.አይ.ኤስ ላይ የቤት ቁጥር፣ ብሎክና ፓርሴል 000 የተባሉ ወይም ያልተሰጣቸው ይዞታዎች መስተንግዶ አሰጣጥ፡-
ትራንስፎርምድ በተደረገው ጂ.አይ.ኤስ ላይ ብሎክ፣ የቤት ቁጥርና ፓርሴል ቁጥር የሌለ ከሆነና ትራንስፎርምድ ባልተደረገው ጂ.አይ.ኤስ ላይ መረጃው ካለ በሲ.አይ.ኤስ የመረጃ ቋት ውስጥ የሚገኘው ብሎክ፣ ፓርሴልና የቤት ቁጥር እየተገናዘበ ተመሳሳይ መሆኑ ሲረጋገጥ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡
በየደረጃው ላሉ ለተቀናጀ የመሬት መረጃ ማዕከል ተቋም እንዲያውቀው በደብዳቤ ይገለጻል፡፡
ትራንስፎርምድ በተደረገው ጂ.አይ.ኤስ ላይ ወይም ባልተደረገው ጂ.አይ.ኤስ ላይ ብሎክ፣ የቤት ቁጥርና ፓርሴል ያልተሰጣቸው ሆኖ በሲ.አይ.ኤስ የመረጃ ቋት ላይ ብሎክ፣ ፓርሴልና የቤት ቁጥር ያላቸው ከሆነና ይዞታውና ቤቱ ግንቦት 1988ዓ.ም በፊት መኖሩ በሶፍራቶፕ፣ በኖርቴክና ጂ.አይ.ኤስ ላይ በትክክል እስከተረጋገጠ ድረስ በሲ.አይ.ኤስ የመረጃ ቋት ላይ የሚገኘውን ብሎክ፣ ፓርሴልና የቤት ቁጥር መረጃ መሰረት ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ይዘጋጅላቸዋል፡፡
ነገር ግን ይዞታው ከግንቦት 1988 ዓ.ም በፊት የተያዘና ቦታው ላይ ቤት ስለመገንባቱ በሶፍራቶፕ ማፕ ወይም በኖርቴክ ወይም ጂ.አይ.ኤስ ቢረጋገጥም በሲ.አይ.ኤስ ወይም ጂ.አይ.ኤስ መረጃ ላይ ብሎክ፣ ፓርሴልና የቤት ቁጥር መረጃ የሌለው ከሆነ ለወረዳው ከተሰጠው ብሎክ ከመጨረሻው ቁጥር ቀጥሎ በመስጠት፣ ፓርሴል የሌለው ከሆነ ከብሎኩ ከመጨረሻ ፓርሴል ቁጥር ቀጥሎ በክ/ከተማው የሰነድ አልባ ይዞታዎች መስተንግዶ ፕ/ዴስክ በኩል በመስጠት በዚሁ መመሪያ ስለ መረጃ እርማት በተቀመጠው አግባብ ታይቶ መረጃው ሲስተካከል ህጋዊ የይዞታ ማረጋጫ ካርታ የሚዘጋጅለት ይሆናል፡፡
መጋቢት 9/2014 ዓ.ም(ሲሳይ ሰማኝ)

Comments

Be the first to add a comment