ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 3,775 የላብራቶሪ ምርመራ 185 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4848 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 47 ወንድ እና 138 ሴት ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸው ከ3 ወር - 80 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 184 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 1 የውጭ ዜጋ ነው።

160 ሰዎች ከአዲስ አበባ (105 ሰዎች ተመላሾች እና በማቆያ የነበሩ) ፣ 7 ሰዎች ከደቡብ ክልል ፣ 7 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 2 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 2 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 1 ሰው ከትግራይ ክልል፣ 1 ሰው ከጋምቤላ ክልል እና 1 ሰው ከሐረሪ ክልል ናቸው።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 30 (11 ከጤና ተቋም እና 19 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ናሙና የለም።

@tenaET | tena.et/update

Comments

Be the first to add a comment