የኢትዮጵያ መንግስት ሠራተኞች የጡረታ መመሪያ!
***
የመንግስት ሠራተኞች የጡረታ በእድሜ (60 ዓመት ሲሞላ) ሲሆን በማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ  ሠራተኛው የጡረታ ምዝገባ ማድረግ እንዳለበት ተደንግጓል

1. የምዝገባ ሂደት

ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ ከተቀጠረ በ60 ቀናት ውስጥ በማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ የጡረታ ምዝገባ ማድረግ አለበት።

2. የጡረታ መዋጮ

● ለሲቪል ሰራተኞች: ከሰራተኛው 7%፣ ከመንግስት 11% ሲሆን፣ በድምሩ 18% ይሆናል።

● ለፖሊስና ለመከላከያ ሰራዊት: ከሰራተኛው 7%፣ ከመንግስት 25% ሲሆን፣ በድምሩ 32% ነው።

3. ለጡረታ የሚያበቁ ምክንያቶች

● በእድሜ ምክንያት (60 ዓመት ሲሞላ)
● በራስ ፍቃድ
● በጤና ጉድለት
● በስራ ላይ በደረሰ የአካል ጉዳት
● በሞት

4. የጡረታ አበል በውክልና የሚከፈልባቸው ሁኔታዎች

● በእርጅና
● በህመም
● ወደ ውጭ አገር በመሄድ
● በትምህርት ወደ ሌላ ቦታ በመሄድ
● በእስራት ምክንያት

5. የጡረታ አበል በይርጋ የሚዘጋበት ጊዜ

● የጡረታ ጥያቄ ሳይቀርብ ወይም የተወሰነ የጡረታ አበል ሳይወሰድ ከ3 ዓመት በላይ ከቆየ፣ አይከፈልም። ነገር ግን፣ ከዚያ በኋላ ጥያቄ ካቀረበ፣ ከአመለከተበት ቀን ጀምሮ ክፍያው ይቀጥላል።

○ የሟች ጡረታ (ዳራጎት) ሳይጠየቅ ወይም ለ3 ዓመት ሳይወሰድ ከቆየ፣ በይርጋ ይዘጋል።

6. በእድሜ ምክንያት ለሚወጣ ሰራተኛ የጡረታ ስሌት

● የጡረታ አበል የሚሰላው በመጨረሻዎቹ 36 ወራት (3 ዓመት) አማካይ ደመወዝ ላይ ተመስርቶ ነው።

● ከመጀመሪያው የቅጥር ቀን እስከ 10 ዓመት ያለው አገልግሎት በ30% ይባዛል።

● ከ10 ዓመት በላይ ያለው እያንዳንዱ ተጨማሪ የአገልግሎት ዓመት በ1.25% ይባዛል።

○ ለምሳሌ: 28 ዓመት ያገለገለ ሰራተኛ ስሌት፡-

● (10 ዓመት × 30%) + (18 ዓመት × 1.25%) = 30% + 22.5% = 52.5%

● የመጨረሻ 36 ወራት አማካይ ደመወዝ 5,000 ብር ከሆነ፣ የጡረታ አበሉ 52.5% × 5,000 ብር = 2,625 ብር ይሆናል።

7. የቅጥር ቀንና ወር ሲታጣ
የቅጥር ዘመን ብቻ በህይወት ታሪክ ከተሞላ፣ የጡረታ ቀንና ወር በሚከተለው መልኩ ይያዛል፡-

● በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከሆነ ነሐሴ 30 ተብሎ ይወሰዳል።

● በግሪጎሪያን (እ.ኤ.አ) አቆጣጠር ከሆነ ታህሳስ 31 ተብሎ ይወሰዳል።

8. በራስ ፈቃድ ጡረታ መውጣት

● አንድ ሰራተኛ እድሜው 55 ዓመት ሲሆን እና የ25 ዓመት የአገልግሎት ዘመን ሲኖረው በራሱ ፍላጎት ጡረታ መውጣት ይችላል።

● ለፖሊስና ለመከላከያ ሰራዊት ግን ጡረታ ከሚወጡበት እድሜ 5 ዓመት ቀድመው መውጣት ይችላሉ።

9. የሟች ጡረታ ወራሾች

● የሟች ጡረታ የሚወርሱ ልጆች እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ወይም የአካል ጉዳተኛ ልጅ ከሆነ ከ21 ዓመት በታች መሆን አለባቸው።

● የሟች እናትና አባትም ወራሾች ይሆናሉ።

10. ለጡረታ አበል ማስፈፀሚያ የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች

● የህይወት ታሪክ ቅጽ (ጡ1 እና ጡ2)
● የሙከራ እና የቋሚ ቅጥር ደብዳቤዎች
● የጡረታ መለያ ቁጥር
● የ36 ወራት ደመወዝ መረጃ
● የዝውውር፣ የደረጃ እድገት እና የደመወዝ ለውጥ ደብዳቤዎች
● የጋብቻ እና የልጆች ማስረጃ
● የባለጡረታው ወይም የወራሽ ፎቶግራፍ!

Comments

Be the first to add a comment