👉የግንባታ ፍቃድ እና የግንባታ ፕላን

💫በኢትዮጵያ የሕንጻ አዋጅ ቁጥር 624/20001 እና በሚኒስቴሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 243/2003 (አንቀጽ 2(8)) መሰረት፦

⭐️የግንባታ ፍቃድ ማለት አንድ የሕንጻ ግንባታ ለማካሄድ ለሚፈልግ አካል ሕንጻውን ለመገንባት የሚያስችሉት ዝርዝር መስፈርቶች እንደተሟሉ በከተማው (ሕንጻ) ሹም ተረጋግጦ ግንባታ እንዲካሄድ ፍቃድ መስጠቱን የሚገልጽ ማስረጃ ማለት ነው።

🚧ፕላን ማለት ደግሞ በአዋጁ አንቀጽ 2(15) ሥር እንደተጠቀሰው የአንድ ሕንጻ መጠን፣ ቅርጽ፣ ስፋት እና አይነት የሚያሳይ ሆኖ ሕንጻው የሚሰራበትን ቁሳቁስ /ግብአት/ እና የአገነባብ ዘዴን የሚያሳይ ንድፍ ወይም ሞዴል ሲሆን የአርክቴክቸራል፣ ስትራክቸራል፣ ሳኒተሪ፣ ኤሌክትሪካል፣ መካኒካል፣ የእሳት መከላከል እና ሌሎች አስፈላጊ ሥራዎችን የሚያሳይ ንድፍ የሚያካትት ማለት ነው።

💫የ YouTube ቻናላችን👇

https://www.youtube.com/@EthiopianConstruction7

@etconp

Comments

Be the first to add a comment