የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
ዕርቅ
ውድ የቻናላችን ተከታታዬቻችን ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ስለ ዕርቅ ይዤላችሁ ቀርቤላችሁዋል መልካም ንባባብ
• በፍርድ ቤት በመካሄድ ላይ ያለ ክርክር ለማቋረጥ ተከራካሪ ወገኖች የሚያደርጉት ስምምነት
እርቅ በፍርድ ቤት ሊፀድቅ የሚችለው ጉዳዩ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት በመታየት ሂደት ላይ እያለ ተከራካሪ ወገኖች ጉዳዩን በስምምነት የጨረሱ መሆኑን ገልፀው ይኼው ስምምነታቸው ለሕግ እና ለሞራል ተቃራኒ ያለመሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ እርቁ ወይም ስምምነቱ በፍርድ ቤት ተመዝግቦ ክርክሩ እንዲቆምላቸው ሲያመለክቱ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 277 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ያሳያል፡፡ ከዚህ ውጪ ከፍርድ ቤት ውጪ በሚደረግ እርቅ ወይም ግልግል መሰረት ያለመግባባትን ያስቀሩ ወይም ለጉዳያቸው እልባት ያገኙ ሰዎች እርቁ ወይም ግልግሉ እንደተፈረደ ፍርድ ሊቆጠርላቸው የሚገባ እና በውጤቱም በፍርድ ቤት ማስመዝገብ ወይም ማስፀደቅ ሳያስፈልገው ራሱን ችሎ ሊፈጸም የሚችል ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 3312 እና 3324 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 85873 ቅጽ 15፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 277፣
ምንጭ
ሰበር መዝገብ
ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ
ከኢንተርኔት.
Comments
Be the first to add a comment