▢ ከፊሉ ልጅ የለኝም ብሎ ያለቅሳል። ሌላውን ልጁ ያስለቅሰዋል።
ከፊሉ እህት ወንድም የለኝም ብሎ ይከፋዋል።
ሌላው በእህት በወንድሞቹ ውስጡ ቆስሏል።
ዱንያ አጃዒቧ አያልቅም። ግማሹ በመከራ፣ ሌላው በጥጋብ ያለቅሳል።
"
እናቱ የሞተችበትና፣ ገበያ የሄደችበት እኩል ያለቅሳል" በሚለው አገርኛ ብሂል ውስጥ ህመም አለ። መከራ ሁሉ አንድ አይደለም። ከባሰም በላይ ብዙ የባሰ እንዳለ በማስተዋል "
አልሐምዱ ሊላህ" እንበል።
© IbnuMunewor
🌱 @TewhedandSuna