ሰላም! እንደው ቸር ከርማችኋል?
ትንሽ ስለደመወዝ ልናወጋችሁ ብቅ ብለናል። ቀድሞ ነገር ግን “ደመወዝ” ምንድን ነው?
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 56/2010 በአንቀጽ 2 ንኡስ አንቀጽ 12 ላይ “ደመወዝ” ለሚለው ቃል የሚከተለውን ትርጓሜ ሰጥቶታል፥
“ደመወዝ” ማለት በአንድ የሥራ ደረጃ ለተመደቡ ሥራዎች የተወሰነ መነሻ ክፍያ ወይም የእርከን ክፍያ ነው”
ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት በየወሩ መጨረሻ ለሠራተኞቹ ወይም ለሕጋዊ ወኪሎቻቸው የደመወዝ ክፍያ የመፈጸም ግዴታ ያለበት ሲሆን እኩል ዋጋ ያላቸው ሥራዎች ሁሉ እኩል መነሻ ደመወዝ ይኖራቸዋል።
ይህን ልብ ይበሉ!
የማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ፥
ሀ) ሠራተኛው ስምምነቱን በጽሁፍ ሲገልጽ፣
ለ) በፍርድ ቤት ትዕዛዝ፣
ሐ) በሕግ በተደነገገው መሠረት
ካልሆነ በስተቀር ሊያዝ ወይም ሊቆረጥ አይችልም።
በፍርድ ቤት ውሳኔ ወይም በሕግ መሠረት ከሠራተኛ ደመወዝ በየወሩ የሚቆረጠውም ቢሆን ከደመወዙ አንድ ሦስተኛ አይበልጥም።

ህዳር 17 ቀን 2015 ኣ.ም
ፋሲካ አጌና (የህ/ስ/ም/መ/ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ አቃቤ-ሕግ)

Comments

Be the first to add a comment