ለሜሲ የተገነባው 70 ቶን የሚመዝነው ሃውልት
ነገሩ እንዲህ ነው... በአርጀንቲናዋ ኒውኩዌን ግዛት የምትገኘው ኩትራል ኮ የተባለች ከተማ በሀገሪቱ የ"ሐውልቶች ዋና ከተማ" በመባል ትታወቃለች። እናም ይህች ከተማ ከሰሞኑ መላው ዓለምን ያስገረመ፣ ለሊዮኔል ሜሲ የሚመጥን ግዙፍ የክብር መግለጫ ይፋ አድርጋለች።
አርቲስት አልዶ ቤሮይሳ የተባለ የሀገር በቀል መሃንዲስና ቀራፂ ሌት ተቀን ደክሞ፣ ከብረት ማገርና ከከባድ ኮንክሪት ድንቅ ጥበቡን ከትቦታል።
ሜሲ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ድል ማግስት የወርቅ ዋንጫዋን አንስቶ በኩራት ወደ ሰማይ ቀና ያለበትን ምስል ነው - በ26 ሜትር ከፍታ እና በ70 ቶን ክብደት በኮንክሪት የፈለፈለው።
ቁመቱና ክብደቱ ያስፈራል! በብሔራዊ አውራ ጎዳና ቁጥር 22 አጠገብ የቆመው ይህ ሐውልት፣ አሁን በዓለማችን ላይ ለአንድ እግር ኳስ ተጫዋች የቆመ ትልቁና ረጅሙ ሐውልት ሆኖ ተመዝግቧል።
ከዚህ ቀደም ህንድ ኮልካታ ላይ ቆሞ የነበረው የ21 ሜትር የሜሲ ሐውልት በትልቅነቱ ይታወቅ ነበር። ነገር ግን በነፋስ የመወዝወዝ እና የደህንነት ስጋት ስላመጣ እንዲፈርስ ተደርጓል።
የአርጀንቲናዎቹ ግን በኮንክሪት የጸና በመሆኑ "ንቅንቅ የለም" የሚል ይመስላል።
ይህ ሐውልት በተመረቀበት ሰሞን ሜሲ በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ሜዳ ላይ ታሪክን በአዲስ መልክ እየጻፈ ነው።
በምድብ ጨዋታዎች ላይ በአልጄሪያ ላይ ሀት-ትሪክ (3 ጎል)፣ በኦስትሪያ ላይ ደግሞ 2 ጎሎችን አስቆጥሮ አርጀንቲናን ወደ ጥራው ጨዋታ (Knockout Stage) መርቷታል። በዚህም በዓለም ዋንጫ ታሪክ 18 ጎሎችን በማስቆጠር የጀርመኑን ሚሮስላቭ ክሎዜን ክብር ሰብሮ የዓለም ዋንጫ የምንጊዜውም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኗል።
የብራዚሉ ታሪክ ነሺ ሮናልዶ ናዛሪዮ ሳይቀር "እንግዲህ ክርክሩ ያብቃ፣ ሜሲ የምንጊዜውም ምርጡ ነው" ብሎ እጅ እንዲሰጥ ያደረገ አጨዋወት።
ከጀርባው ግን የአባቱ መታመም የፈጠረበት የውስጥ ስብራትና የእንባ ማዕበልም አለ።
ያም ሆነ ይህ፣ ሜሲ ዛሬ በዓለም እግር ኳስ ሰማይ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በአርጀንቲና አውራ ጎዳናዎችም ላይ እንደ ተራራ ገዝፎ ይታያል።
የኮንክሪቱ ሐውልትና የሜዳው ላይ ክብር ተዳምረው የዘመናችንን የእግር ኳስ ንጉሥ ዝና ይበልጥ አጣፍጠውታል።
@etconp