👉በሳይት ላይ የሚያጋጥም ከባድ መዋቅራዊ አደጋ፦ Column Buckling Failure⚠️🏗️

🌟​በምስሉ ላይ እንደምናየው የተጠናከረ ኮንክሪት አምድ (RC Column) ከባድ የቦታ መፈናቀል እና የመታጠፍ (Buckling) አደጋ አጋጥሞታል።

☄ይህ አይነቱ አደጋ ሙሉ ህንፃውን ለውድቀት (Catastrophic Collapse) ሊዳርግ የሚችል አደገኛ ሁኔታ ነው።

🏛​ለ Column Buckling መንስኤ የሚሆኑ 3 ዋና ዋና ነጥቦች፦

1. ​High Slenderness Ratio (የረጅም አምድ ሁኔታ)፦ የኮለሙ ርዝመት ከስፋቱ አንጻር አላስፈላጊ በሆነ ሁኔታ ረጅም ሲሆን (Slender Column) የመታጠፍ እድሉ ይጨምራል።

2. ​Inadequate Lateral Ties (የካንሰል ብረት አነስተኛነት/ርቀት)፦ የካንሰል ብረቶች ርቀት (Stirrup Spacing) ከተፈቀደው በላይ ሰፊ ሲሆን ዋናዎቹን የ ቁም ብረቶች (Main Longitudinal Rebars) አግዶ የመያዝ አቅማቸው ይቀንሳል።

3. ​Eccentric Loading & Poor Concrete Quality፦ ጭነቱ ከመካከለኛ መስመር (Centerline) ውጪ ማረፍ ወይም የኮንክሪት ጥራት ማነስ (Honeycombing)።

🚥​በእርስዎ ሳይት ላይ ረጅም ኮለሞችን (Slender Columns) ሲነድፉ ወይም ሲሰሩ Bucklingን ለመከላከል የሚያደርጉት ዋነኛ ጥንቃቄ ምንድን ነው? ሃሳብዎን በኮሜንት ያካፍሉን

​💡ተመሳሳይ ሙያዊ የሳይት ኢንጂነሪንግ መረጃዎችን ለማግኘት የ YouTube ገጻችንን Subscribe ያድርጉ👇

https://youtube.com/@ethiopianconstruction7?si=ils307xXQQpIdCwG

@etconp

Comments

Be the first to add a comment