✿
ውሀ ሻጭ? ¤ አንድ ሰው መንገድ ላይ እያዞረም ይሁን፣ ሱቅም ይክፈትለት፣ ሆቴልም ላይ ይደርድረው፣ ትምህርት ቤት፣ መስጂድ፣ ጤና ጣቢያ፣ ሌሎችም ቦታዎች ላይ ውሀን በማቅረብ ገቢ ካገኘ ውሀ ሻጭ ወይም ውሀ ይሸጣል መባሉ ትክክለኛ ስራውን ወይም ገቢውን ይገልፃል፡፡
መንደር ላይ ለዉዱእ በሃይላንድ የሚሸጠውም ሆቴል ላይ በውድ የሚሸጠውም “ውሀ ሸጡ” ነው የሚባለው፡፡ መያዣ እቃው ቢለያይ፣ ማርኬቲንጉ ከፍ እና ዝቅ ቢል፣ የቧንቧም ይሁን የሃይላንድ የተሸጠው ውሀ ነው፡፡ ውሀ!!
ወሬው ስለ ውሀ እንዳልሆነ አይጠፋችሁም!!!
አንድ ወንድ መስራት እየቻለ መስጂድ ላይ ቆሞም ቢጠይቅ፣ መንገድ ላይ ለማስመጥም ቢሞክር፣ ሚዲያ ላይ አካውንትም ቢለጥፍ፣ ሌላም ስም ይስጠው መስራት እየቻለ ክብሩን አውርዶ እየለመነ ነው፡፡ እየለመነ!!
ቦታው ስለተቀያየረ፣ አጠያየቁ ስላማረ ከልመናነት አይወገድም፡፡ ክብርን ሽጦ ልመና!
ሴቷም ብትሆን መንደር ላይም ይሁን፣ ሆቴልም ትሂድ፣ ሚዲያም ላይ በውበቷና ጭፈራ ትውጣ፣ ዋጋው ከፍም ይበል ዝቅ፣ ክብሯን(ሰውነቷን) በመጠቀም ገንዘብ ከሰራች ክብሯን ሽጣለች፡፡
የክብሩ ደረጃ የከፋም ይሁን ሻል ያለ ክብር እና ሐያእ ተሽጧል፡፡ ክብርን ሽጦ ሽቀላ!
©huneynn
🌱 @TewhedandSuna