👉ማስታወቂያ

💫የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት እየተገበረ ለሚገኝው መጠነ ሰፊ የቤት ልማት ፕሮግራም በግንባታው ዘርፍ ላይ የተሰማሩ እና መስፈርቱን የሚያሟሉ ስራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይጋብዛል ፡፡

🏷በዚህም መነሻ

1. ለስራ ተቋራጮች ምዝገባ መሟላት
ያለባቸው መረጃዎች፡-

ሀ) የታደሰ የንግድ ፍቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገቡ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤

⏺በምዝገባው ወቅት የሰነዶቹን ዋና እና አንድ የማይመለስ ቅጂ በአካል የሚቀርብ ሆኖ የስራ ተቋራጩ የበላይ ኃላፊ ባለቤት ወይም ህጋዊ ውክልና ያለው ተወካይ ፊርማ እና የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

2. ደረጃ 1 እና 2 (ህንፃ (BC) እና ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ(GC)) እንዲሁም ደረጃ- 3 (ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ (GC)) የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው በግንባታው ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ስራ ተቋራጮች ተሳታፊ መሆን ይችላሉ

3. ከዓርብ ሚያዝያ 30 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ቅዳሜን ጨምሮ ለ5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ( እስከ ዕሮብ ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ/ም ከሰዓት እስከ 11፡30)) በአካል በመቅረብ በኮርፖሬሽኑ 11ኛ ወለል በሚገኝ አዳራሽ ላይ ምዝገባ በማድረግ መረጃዎቹ መሟላታቸው በመዝጋቢው ሲረጋገጥ ለዚሁ የተዘጋጀ የቴክኒካል ሰነድ መግዛት ይቻላል፤

4. ተገቢውን ሰነድ በማቅረብ የምዝገባ ሂደቱን በሚገባ ያሟላ ስራ ተቋራጮችን በተመለከተ ምዝገባው በተጠናቀቀ በ 24 ሰዓት ውስጥ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ/ም በተቋሙ ማህበራዊ ድህረ ገጽ እና በኮርፖሬሽኑ የማስታወቂያ ቦርድ 11ኛ ወለል የሚለጠፍ ይሆናል፡፡

5. ስራ ተቋራጮች የቅድመ ምዝገባ ውጤት ከታወቀበት ቀን ቅዳሜን ጨምሮ በአስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ቅጂ የቴክኒካል ፕሮፖዛላችሁን ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን እስከ ቀን ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከሰዓት 10፡00 ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. ስራ ተቋራጮች ለምዝገባ እና ለቴክኒካል ሰነድ ግዢ የማይመለስ ብር

ለደረጃ 1 ...........ብር 7500
ለደረጃ 2 .......... ብር 6500
ለደረጃ 3 ...........ብር 5500 መክፈል ይጠበቅባቸዋል፡፡

📍አድራሻ:-ቂርቆስ ክ/ተማ ወረዳ 01
ባምቢስ አከባቢ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ህንፃ ላይ

ሚያዝያ 29 ቀን 2018 ዓ/ም

@etconp

Comments

Be the first to add a comment