የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
ሐሰተኛ ሰነዶችን መፍጠር፤ ሰነዶችን ወደ ሐሰተኛነት መለወጥና ማጥፋት
በግዙፍ የሚፈጸም ሐሰት
ማንም ሰዉ የሌላዉን ሰዉ መብት ወይም ጥቅም ለመጉዳት ወይም ለራሱ ወይም ለሌላ ሰዉ ተገቢ ያልሆነ ማናቸዉንም መብት ወይም ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት በማሰብ፡-
ሕጋዊ ክርክሮች ሲካሄዱ በማስረጃነት የሚቀርቡ አንድን ፍሬ ነገር ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ወይም የሚያረጋግጡ የሚመስሉ እንደ ጽሁፍ፤ ሌሎች ሰነዶች ወይም ግዙፍ ነገሮች የመሳሰሉትን የፈጠረ እንደሆነ ወይም፤
ሐሰተኛ ሰነድ ለማዘጋጀት በሌላ ሰዉ የጣት ፊርማ፤ ፊርማ ፤ ምልክት ወይም ማሕተም የተጠቀመ እንደሆነ ወይም፤
እዉነተኛዉን ጽሁፍ በመለወጥ ወይም በመደለዝ በሐሰተኛ ፊርማ በእጅ በተደረገ ምልክት ወይም በጣት ፊርማ፤ በማህተም ወይም የሌለዉን ሥልጣን ወይም ችሎታ እንዳለዉ አስመስሎ በመፈረም ሐሰተኛ ሰነድ የፈጠረ እንደሆነ ወይም፤
አንድን ሰነድ፤ በተለይም የፈራሚዉን ስም ወይም ፊርማ ወይም የሰነዱን ይዘት፤ አሀዝ ፍሬ ነገር ወይም ዝርዝር መግለጫ በሙሉ ወይም በከፊል በመለወጥ፤ በማሻሻል በመቀነስ ወይም በመጨመር ወይም በማጥፋት ወደ ሐሰተኛነት የለወጠ እንደሆነ ከሦስት ወር በማያንስ ቀላል እሥራት ወይም ነገሩ በጣም ከባድ በሆነ ጊዜ ከአሥር ዓመት በማይመልጥ ጽኑ እስራት ይቀጣል፡፡
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 375
ህድአት ጌታቸዉ የካቲት/2013 ዓ.ም
Comments
Be the first to add a comment