👉የጨረታ ማስከበሪያ (bid security/bond) ገንዘብ መጠን አወሳሰን

🚧አዲሱ የመንግስት ግዢ መመሪያ የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ አወሳሰንን በተመለከተ «የመንግስት መ/ቤቱ የጠቅላላ ግዥውን ግምታዊ ዋጋ መሰረት በማድረግ ከ 0.5% ያላነሰ እና ከ 2% ያለልበለጠ የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን ወስኖ በጨረታው ጥሪው እና በጨረታ ሰነዱ ውስጥ መግለፅ ይኖርበታል፡፡

በዚህ መሠረት የሚወሰነው የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከብር 2,000,000 (ሁለት ሚሊዮን ብር) የበለጠ መሆን የለበትም
» የሚል ድንጋጌ አስቀምጧል።

በመሆኑም በአንድ የጨረታ መጥሪያ (Tender notice) ወይም በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተቀመጠው የጨረታ ማስከበሪያ ከ 0.5% ያነሰ ወይም ከ2% የበለጠ ከሆነ፣ በየትኛውም መልኩ ደግሞ ከ 2,000,000 ብር ከበለጠ ጨረታውን ሊያሰርዝ ይችላል።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment