✿ ወዳጄ የሰው ልጅ ልክ እንደ ተራራ ነው …

ጥንካሬው በማይታየው ድብቅ ማንነቱ ውስጥ ነው ያለው። ጂኦሎጂስቶች እንደሚሉት “አንድ ተራራ ከሙሉ መጠኑ አንድ ሦስተኛ ክፍሉ ብቻ ነው ለኛ የሚታየን። ሁለት ሦስተኛው ክፍሉ ከመሬት ስር የተቀበረ ነው።

 እኛም እንዲሁ ነን!
የምንደብቀው ማንነታችን  ከምናሳየው በላይ ነው። በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ ተቀበለውም ካደው፣ደበቀውም ይፋ አወጣው፤ የተዳፈነ ህመም አለው! ከላይ በምታየው ብቻ ተንተርሰህ ፍርድ ለመስጠት አትቸኩል፤ ነገሮች ለኛ መስለው እንደሚታዩን አይደሉም!

በሰላማዊ ሕይወቱ የምትቀናበት የተረጋጋ ሚመስልህ ሰው፤ በልቡ ውስጥ አላህ ብቻ የሚያውቀው ነበልባል እሳት ሊኖር ይችላል።
ጭስ ስላልወጣው፣እየተቃጠለ አይደለም ማለት አይቻልም !!!!


🌱 @TewhedandSuna

Comments

Be the first to add a comment