🫵የሴፍቲ ቀን የማለዳ መልእክት

​📥 ክፍል 1፦ "አንድ ስህተት የመጨረሻ ሊሆን ይችላል!"

🚧​ርዕስ፦ በከፍታ ላይ የሚሰሩ ስራዎች እና የሴፍቲ ቤልት (Safety Harness) እውነታዎች ⚠️

❇️​የባለ ብዙ ፎቅ ሕንጻዎች ግንባታ ላይ ስራዎች ሲፋጠኑ፣ አደጋዎች የሚከሰቱት በሴኮንዶች ሽርፍራፊ ውስጥ ነው።

🔗በኮንስትራክሽን ሳይት ላይ "ለጥቂት ደቂቃ እኮ ነው" በሚል ቸልተኝነት የሴፍቲ ቤልት (Safety Harness) አለማሰር የህይወት ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል።

​🚧 የሴፍቲ ቤልት እንዲሁ የሚታጠቅ ጌጥ አይደለም!

• ​ሳይት ላይ ከመውጣትህ በፊት ቤልቱ በትክክል መስራቱንና አለመቀደዱን አረጋግጥ።
• ​ሁልጊዜም አስተማማኝና ጠንካራ በሆነ ቦታ ላይ (Anchor Point) ብቻ አጥምደው።
• ​"እኔ ጎበዝ ነኝ፣ አልወድቅም" የሚል መተማመንን አስወግድ፤ ከፍታ ላይ ስህተት አንድ ጊዜ ብቻ ነው የሚፈቀደው።

🏷ዛሬ በሳይታችን ላይ ሁላችንም ቆም ብለን እንጠይቅ፦ "ከፍታ ላይ ስንሰራ ሙሉ በሙሉ ደህንነታችን የተጠበቀ ነው?" ስህተት ከመፈጠሩ በፊት ዛሬ ክፍተቶቻችንን በጋራ እንለይ።

ህይወት መተኪያ የላትም‼️

@etconp

Comments

Be the first to add a comment