👉ይህ ቦታ በዱባይ Al Warsan ተብሎ በሚጠራ የከተማው ክፍል በ800 ሄክታር መሬት ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኝ አስደናቂ የሪል ስቴት ግንባታን የሚያሳይ ሥራ ነው።

💫Nakheel property በተባለ የሪል ስቴት ገንቢ ድርጅት የተገነባው ይህ መንደር፣ መገኛው ከዱባይ አለም አቀፍ ኤርፖርት 9 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው።

🚧መጠሪያው ደግሞ International City ይባላል።

🏷የዚህ ግዙፍ መንደር ልማት የተካሄደው በተለያዩ ክላስተሮች ተከፋፍሎ ነው።

⏺እያንዳንዱ ክላስተር የራሱ መጠሪያ አለው የቻይና ሰፈር፣ የኢንግሊዝ መንደር፣ የስፔን ግቢ፣ የፈረንሳይ እና የሞሮኮ ሰፈሮችም በጥቂቱ የሚጠቀሱ ቦታዎችም ይገኙበታል።
⏺አካባቢው የመኖሪያና የንግድ ሥራዎች የሚካሄዱበት ሲሆን፣ በዘመናዊ እና በፕላን ከመገንባቱ በተጨማሪ ማራኪ ኪነ ሕንፃን ከመሆኑም በላይ እያንዳንዱ ሕንፃ እና ሰፈር የተለያዩ ሀገሮች የግንባታ ይዘትን እንዲወክል ተደርጎ የተገነባ ዘመናዊ መንደር ነው።

Via ኢንፍራኮን ሚዲያ


@etconp

Comments

Be the first to add a comment