👉የአዋሽ - ኮምቦልቻ - ሐራ ገበያ እና የሐራ ገበያ - መቀሌ የባቡር መስመሮች ግንባታ ሊጀምር ነው ተባለ

🚆 የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ በ2013 ዓ.ም በሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ግጭት ምክንያት ግንባታቸው ተቋርጠው የነበሩትን የባቡር መንገዶች ግንባታ ለማስጀመር የሚያስችሉ ግምገማዎች ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡

🏷ማዕከላዊ ኢትዮጵያን ከሰሜን ጋር ለማገናኘት የተነደፉት የባቡር መስመሮቹ፦

🔶 የአዋሽ - ኮምቦልቻ - ሐራ ገበያ 392 ኪሎ ሜትር፣
🔶 የሐራ ገበያ - መቀሌ 268 ኪሎ ሜትር ርዝመት አላቸው፡፡

💫ፕሮጀክቶቹ፣ የቻይና የፋይናንስ ተቋማትን ጨምሮ በአብዛኛው በውጭ ብድር የሚሠሩ መሆናቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

🛤 ኮርፖሬሽኑ በዓመቱ ውስጥ ከግንባታ ፕሮጀክቶች እና ከሌሎች የንግድ እንቅስቃሴዎች 710 ሚሊዮን ብር ገቢ ቢያገኝም፣ ከባቡር ሐዲድ ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ በውጭ ዕዳ ጫና ውስጥ እንደሚገኝ ግምገማው ላይ ተጠቅሷል፡፡

@etconp

Comments

Be the first to add a comment