የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 56/2010 ዓ.ም
የመንግስት ሰራተኛ ምን ማለት ነዉ?
“የመንግሥት ሠራተኛ” ማለት በአስተዳደሩ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ በቋሚነት ተቀጥሮ የሚሰራ ሰው ነው። ነገር ግን በአስተዳደሩ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ የተቀጠሩ ቢሆንም በዚህ አዋጅ የማይገዙ ተቀጣሪዎች አሉ።
የመንግስት ሰራተኛ ለመሆን መሟላት ያለባቸዉ ሁኔታዎች
አንድ ሰዉ በአስተዳደሩ ስር የሚገኝ መስሪያ ቤት ዉስጥ ተቀጥሮ ለመስራት፦
• ዕዴሜው ከ 18 ዓመት በላይ የሆነ ሰው፤ ነገር ግን ከ 14 አመት በላይ የሆናቸዉ ልጆችን ለመቅጠር በመመሪያ ሊወሰን ይችላል
• በሙስና፣ እምነት ማጉደል፣ የስርቆት፣ የማጭበርበር ወይም የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈጽሞ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት የተፈረደበት ማንኛውም ሰው ሆኖ ነገር ግን ቅጣቱ ከተፈጸመ፣ በይርጋ ከታገደ ወይም በይቅርታ ከተሰረዘ 5 አመት ያለፈው እና ከነዚህ ወንጀሎች ነፃ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት። ከዚህ ወንጀል ዉጪ በዚህ አዋጅ አንቀፅ 88 መሰረት በዲሲፒሊን ከመንግሥት መስሪያ ቤት ከስራ ተሰናብቶ አምስት አመት የሞላዉ ሰው።
• የብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
• በዚህ አዋጅ አንቀጽ 17 መሠረት ቃለ-መሀላ ለመፈጸም ፈቃደኛ የሆነ ሰው፡፡
• ከኤች አይ ቪ ውጪ ማንኛውንም ምርመራ ለማድረግ ፈቃደኛ የሆነ
• ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነ። ነገር ግን ኢትዮጵያዊ ለተፈለገዉ ስራ ማግኘት ካልተቻለና የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎችን በትውልድ አገራቸው በተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ ለማድረግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 270/1994 አንቀፅ 5(2) በተደነገገው በጊዚያዊነት መቅጠር ይቻላል።
የመንግስት መስሪያ ቤት ያለበት ግዴታ
• ግንዛቤ ፈጠራ
• የስራ ቦታ ከሃይማኖት የጸዳ ማድረግ
• ለሰራተኛው የስራ ሃላፊነቱን በዝርዝር ማሳወቅ
• ስራን በእቅድ እንዲመራ በማድረግ አፈጻጸሙንም በዚሁ መሰረት መገምገም
• የስራ ቦታን ለሰራተኛዉ መቹ እንዲሆን ማድረግ
• ለስራዉ የሚያገለግሉ መሳሪያዎችን ማቅረብ አገልግሎቱንም ማሳወቅ በማለት በአጭሩ ያስቀምጠዋል
የመንግስት ሰራተኛዉ ያለበት ግዴታ
• አንድ የመንግስት ሰራተኛ፦
• ህገ-መንግስቱን የማክበር እና የማስከበር
• ህግ እና ፖሊሲዎችን የመተግበር
• ስራን በታማኝነት እና በትጋት መፈጸም
• በስራ መዘርዝሩ እና በቅርብ ሃላፊዉ የሚሰጡትን ስራዎች የመተግበር የግል እምነቱን በስራ ቦታ አለማንጸባረቅ
• ያለ አድሎ መስራት
• በስራዉ አጋጣሚ ያገኘዉን መረጃ በሚስጥር መያዝ
• ከስራዉ ጋር የሚቃረን ወይም የሚያጓድል ሌላ ሰራ መስራት
• ስራን ለፖለቲካ ጥቅም አለማዋል
• ለሰጠዉ አገልግሎት ጥቅም ያለው ነገር በምትኩ አለመጠየቅ
• የተሰጠዉን ማንኛዉም አይነት ንብረት በአግባቡ የመያዝ።በንብረቶቹ ላይም ጉዳት ቢደርስ ተጠያቂ የሚሆነዉ በቸልተኝንት ወይም ሆን ብሎ ከሆነ ብቻ ነው።
• ከኤች አይ ቪ ምርመራ ዉጪ ያሉ ምርመራዎች ለማድረግ ፈቃደኛ መሆን
• ስለሥራ አካባቢ ደህንነትና ጤንነት ጥበቃ የወጡ መመሪያዎችን የማክበር ግዴታዎች አሉበት።
የስራ ሰአትና ፍቃድ (አንቀጽ 33-47)
የአመት ፈቃድ
ይህ ፈቃድ የሚሰጠዉ አንድ ሰራተኛ በተሰጠዉ የእረፍት ግዜ እራሱን አነቃቅቶ እና በቂ እረፍት አግኝቶ ወደስራዉ በመመለስ የተሻለ የሥራ አፈጻጸም እንዲኖረዉ ነዉ። እረፍት መዉሰዱም ለአሰሪዉም ሆነ ለሰራተኛው ብዙ ጥቅም ያለዉ ነዉ።
አንድ የመንግስት ሰራተኛ የአመት እረፍት ለማግኘት 11 ወራት ማገልገል አለበት። ፍቃዱም 20 ቀን ብሎ ይጀምራል በየአመቱም 1 ቀን ይጨምራል። ነገር ግን ይህ ጭማሪ 30 ቀን ላይ ሲደርስ ያቆማል።
የአመት እረፍትም ወደ ብር የሚቀየረዉ አገልግሎት ሲቋረጥ ብቻ ነዉ። ከዛ ዉጪ ባለዉ ባስገዳጅ ሁኔታዎች ብቻ በበላይ ሃላፊዉ ተዕዛዝ መሰረት የአመት እረፍት ለ 2 የበጀት አመት ሊራዘም ይችላል።
የአመት ፈቃድ ወደብር የሚለወጠዉ አገልግሎት ሲቀር ብቻ ቢሆንም በበላይ ሃላፊ ለ 2 በጀት አመት እንዲዛወር ከተደረገ እረፍት ዉስጥ የአንዱ በጀት አመት በብር ተለውጦ እንዲሰጥ ለሚቀርብ ጥያቄ መስተንግዶ መሰጠት አለበት።
የቀን ደሞዙም የሚታሰበዉም ያልተጣራዉ ደሞዝ ለ 30 ተካፍሎ ነዉ።
የወሊድ ፍቃድ
- ከወሊድ ጋር በተያያዘ የሚሰጥ ማንኛዉም የሃኪም የእረፍት ትዕዛዝ እንደህመም ፍቃድ ሳይቆጠር ተፈጻሚ ይሆናል።
- የወሊድ ፍቃድ በጠቅላላዉ 120 ቀናት ናቸዉ። 30 ቀናት ግን ከወሊድ በፊት ሊወሰድ ይችላል።
ጽንስ በመቋረጥ የሚሰጥ ፈቃድ
እርግዝናዉ፡-
• 6 ወር ከሞላው — 60 ቀን
• ቅድመ ወሊድ ፍቃድ ሞልታ ከነበር — ተቋርጦ 90 ቀን
• ከ 3-6 ወር እርግዝና — 30 ቀናት
• የአባቶች ፍቃድ 10 የስራ ቀን
የህመም ፍቃድ
- አንድ የመንግስት ሰራተኛ ሃኪም በሚሰጠዉ የእረፍት ትዕዛዝ መሰረት ከክፍያ ጋር እረፍት እንዲወስድ ይፈቀድለታል።
- ጠቅላላ እረፍቱም በአመት ከ 8 ወር በ 4 አመት ከ 12 ወር መብለጥ አይችልም። ለመጀመሪያ 6 ወራትም ከሙሉ ደሞዝ ጋር ለተቀሩት 2 ወራት ከግማሽ ደመወዝ ጋር እረፍቱ ይሰጣል።
- ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ሰራተኛዉ የሙከራ ግዜዉን ያጠናቀቀ መሆን አለበት።
- ሙከራዉን ያላጠናቀቀ ሰራተኛ ከሆነ ከ 1 ወር ላልበለጠ ግዜ ከደመወዝ ጋር ፍቃድ ይሰጠዋል።
- የህመም ፍቃድ የአመት ፍቃድን ያቋርጣል።
ልዩ ልዩ ፍቃዶች
አንድ የምንግስት ሰራትኛ በአንድ የበጀት አመት ዉስጥ፦
• 7 ቀናት ለግል ጉዳዩ ሊወስድ ይችላል።
• ለፍርድ ቤት ቀጠሮ
• ለህዝባዊ ምርጫ
ያለደመወዝ የሚሰጥ እረፍት ፍቃድ
ይህ ፍቃድ በቂ ምክንያት ላቀረበ፣ የምርጫ ተወዳዳሪ ሲሆንና በልዩ የመንግስት ፕሮጀክት ተሳታፊ ሲሆንና ለዲፕሎማቲክ ሚሲዮን ሥራ የሰራተኛ ባል/ሚስት በውጭ ሀገር መመደብ ምክንያት ያለደመወዝ ፍቃድ ይሰጣል፡፡
የስራ ዉል ማቋረጥ እና ማራዘም
- የስራ ዉል በሰራተኛዉ አነሳሽነት ወይም በመንግስት መስሪያ ቤቱ አነሳሽነት ሊቋረጥ ይችላል፡፡
- በመንግስት በኩል በህመም ምክንያት፣ በስራ ፍቃድ ብቃት ማነስ፣ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት፣ በእድሜ እና በሞት ሊቋረጥ ይችላል፡፡
በቦሌ ክ/ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት የሕ/ስ/ም/መ/ዳ ዐቃቤ ሕግ ዉብአለም መስፍን
Comments
Be the first to add a comment