👉በ 28 ሰዓታት ውስጥ የተገነባው ባለ 10 ፎቅ ሕንፃ፦ የዘመናዊው የሞዱላር ግንባታ አብዮት!

​የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በየጊዜው ከምንገምተው በላይ ፈጣን እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እያስተዋወቀ ይገኛል።

ከዚህ በፊት ከዓመታት በላይ ሊፈጅ የሚችለውን የግንባታ ሂደት በሰዓታት ውስጥ ማጠናቀቅ እንደሚቻል ቻይናዊው "ብሮድ ግሩፕ" (Broad Group) ኩባንያ በተግባር አሳይቷል።

•  ​እንዴት ተቻለ? (የሞዱላር ግንባታ ቴክኖሎጂ)፦

◦ ​የሕንፃው አብዛኛዎቹ ክፍሎች እና መዋቅሮች አስቀድመው በፋብሪካ ውስጥ በከፍተኛ ጥራት ተዘጋጅተው (Prefabricated modules) በጭነት መኪናዎች ወደ ግንባታው ቦታ ይወሰዳሉ።
◦ ​ቦታው ላይ ሲደርሱም በክሬኖች (Cranes) አማካኝነት እንደ መጫወቻ ብሎኮች (Lego pieces) እየተደራረቡ እና በቦልቶች እየተጠበቁ፣ የኤሌክትሪክ እና የውሃ ዝርጋታዎች ተጠቃለው በአጭር ጊዜ ውስጥ ሙሉ ሕንፃ እንዲቆም ይደረጋል።
•  ​የዚህ ቴክኖሎጂ ዋና ዋና ጥቅሞች፦

◦ ​ እጅግ እጅግ ፈጣን አፈጻጸም፦ ፕሮጀክቶችን በተቀመጠላቸው እጅግ አጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ።
◦ ​ቀላል እና ጽኑ አቋም፦ በፋብሪካ የሚዘጋጁት የብረት ንጣፎች (Stainless steel modules) ከተለመዱት የኮንክሪት ሰሌዳዎች በበለጠ መልኩ ቀላል ግን እጅግ ጠንካራ በመሆናቸው ለተፈጥሮ አደጋዎች (እንደ ምድር መንቀጥቀጥ) የማይበገሩ እንዲሆኑ ተደርገው የተሰሩ ናቸው።
◦ ​የብክነት መቀነስ፦ በግንባታ ቦታ ላይ የሚከሰተውን የቁሳቁስ ብክነት እና  ውድድር  በእጅጉ ይቀንሳል።

@etconp

1 comment

Tadele Date
how many days takes for productions