👉Constrution Dive የተባለ የመረጃ ተቋም ሰሞኑን 5 construction trends to watch in 2026 በሚል ርዕስ ባሰራጨው መረጃ በ2026 የኮንስትራክሽን ዘርፍ አምስት አዝማሚያዎች (Trends) የሚከተሉት ናቸው ብሏል።

🚧እነዚህ አምስት ነጥቦች ነጥቦች በዋናነት በዓለም አቀፍ ደረጃ (በተለይም በአሜሪካ) ያለውን ሁኔታ መሰረት ያደረጉ ቢሆንም፣ ለዘርፉ ባለሙያዎች ትልቅ መረጃ ይሰጣሉ።


የግብዓት ዕቃዎች ዋጋ መረጋጋት (Stable Material Prices)

እ.ኤ.አ. በ2026 የኮንስትራክሽን ግብዓት ዕቃዎች ዋጋ ላይ ከፍተኛ ጭማሪ ወይም ድንገተኛ ቅናሽ አይጠበቅም። የዋጋ ግሽበቱ ከ2% እስከ 4% ባለው ክልል ውስጥ እንደሚሆን ይገመታል። ይሁን እንጂ እንደ ብረት (Steel) እና አሉሚኒየም ያሉ ምርቶች በታሪፍ (Tariff) ምክንያት ዋጋቸው ከፍ ብሎ ሊቆይ ይችላል።

የሰው ኃይል እጥረት እና የደመወዝ ጭማሪ (Labor Shortages and Rising Wages)

የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት አሁንም ትልቅ ፈተና ሆኖ ይቀጥላል። በዚህም ምክንያት ድርጅቶች ሰራተኞችን ለማቆየት እና አዳዲሶችን ለመሳብ ከፍተኛ ደመወዝ ለመክፈል ይገደዳሉ። ይህም በፕሮጀክቶች አጠቃላይ በጀት ላይ ከግብዓት ዕቃዎች ዋጋ በላይ ጫና ይፈጥራል ተብሎ ይታሰባል።

የመረጃ ማዕከላት እና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች መስፋፋት (Growth in Data Centers and Infrastructure)

የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቴክኖሎጂ እድገት ከፍተኛ የመረጃ ማከማቻ ማዕከላት (Data Centers) ግንባታ እንዲጨምር ያደርጋል። በተጨማሪም መንግስታዊ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች (መንገዶች፣ የኃይል ማመንጫዎች) በ2026 የዘርፉ ዋና አንቀሳቃሽ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

በቴክኖሎጂ የታገዘ አሠራር (Technology Adoption - AI and Robotics)

ውጤታማነትን ለመጨመር እና የሰው ኃይል እጥረትን ለመቋቋም ድርጅቶች በቴክኖሎጂ ላይ የሚያደርጉት ኢንቨስትመንት ይጨምራል።

በተለይም፦
• AI (Artificial Intelligence): ለፕሮጀክት ዕቅድ እና ለዋጋ ግምት።
• Robotics: ተደጋጋሚ እና አድካሚ ስራዎችን በሮቦቶች ማከናወን።
• Drones: የግንባታ ቦታዎችን ለመቆጣጠር እና ዳሰሳ (Survey) ለማድረግ።

ዘላቂነት እና የአካባቢ ጥበቃ (Sustainability and Green Building)

የካርቦን ልቀትን የሚቀንሱ የግንባታ ቁሳቁሶች (ለምሳሌ፡ Low-carbon concrete) እና ኃይል ቆጣቢ የሆኑ የህንጻ ዲዛይኖች ትኩረት ያገኛሉ። አዳዲስ ሕንጻዎችን ከመገንባት ይልቅ ነባር ሕንጻዎችን አድሶ ለሌላ አገልግሎት ማዋል (Adaptive Reuse) እንደ ትልቅ አዝማሚያ ይታያል።


Via Infranco

@etconp

Comments

Be the first to add a comment