👉የመሠረተ-ልማት ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች በሠው ሠራሽ አስተውሎት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሠጠ

የመሠረተ-ልማት ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ዲጅታላይዝ ለማድረግ ታስቦ በሠው ሠራሽ አስተውሎት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሠጥቷል፡፡

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በዓለም ዓቀፍ ደረጃ  ዲጅታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም እየተራቀቀና እየዘመነ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የተቋሙ አመራሮችና ባለሙያዎች ከዘመኑ ጋር ራሳቸውን ፈጥነው በእውቀትና በክህሎት ቀድመው በመገኘት በሀገራችን የሚከናወኑ የመሠረተ-ልማቶች በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ስልጠናው እጅግ የጎላ ነው ያሉት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመሠረተ-ልማት ዘርፍ አማካሪ áŠ á‰ś ቃሲም ጃቢር መድረኩን በከፈቱበት ወቅት ነው፡፡

የሰው ሠልሽ አስተውሎት ያለው ፈፈዳ  በዓለማችንና በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ዘርፍ እጅግ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ  መሆኑን የጠቀሱት ባለሙያው á‹¨á‹•áˆˆá‰ľ ተዕለት ሥራዎችን በማቀላጠፍ አዳዲስ ፈጠራዎችን እውን እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

በተለይ በከተማ ልማት እና መሠረተ ልማት  ዘርፍ የሰው ሠልሽ አስተውሎት (AI) ያለው ጠቀሜ ባለሙያው እንዳብራሩት ዘመናዊ የከተማ ፕላን (Smart City Planning): ሳተላይት እና ድሮኖች የሚሰበስቡትን መረጃ በመጠቀም ከተሞች እንዴት እንደሚያድጉ አስቀድሞ መተንበይ ይቻላል።

ይህም መሬትን በአግባቡ ለመጠቀምና ህገ-ወጥ ሰፈራዎችን ለመቆጣጠር ይረዳል።

የትራንስፖርትና መንገድ አስተዳደር (Traffic Optimization): በትራፊክ መብራቶችና ካሜራዎች አማካኝነት የትራፊክ መጨናነቅን መቆጣጠር እና ተሽከርካሪዎች ያለ ምንም እንከን እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ ይቻላል።

የአገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊነት (E-Governance): እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያሉ አካላት የነዋሪዎችን መረጃና አገልግሎት (ለምሳሌ የሲቪል ምዝገባ) ለማቀላጠፍ በ AI የተደገፉ ዲጂታል ሲስተሞችን እንደምጠቀሙ በስልጠናው ተገልጿል።

Via ከተማና መሰረተ ልማት ሚንስቴር

@etconp

Comments

Be the first to add a comment