🥹
ረመዳን 🌙1️⃣. የቁርአን ወር (شهر القرآن)•አላህ እንዲህ ይላል፦ "የረመዳን ወር ያ ቁርአን በእርሱ ውስጥ የወረደበት ነው።" [በቀራህ፡ 185]
•ጅብሪል (ዐ.ሰ) በየዓመቱ በረመዳን ሌሊቶች ወደ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይመጣና ቁርአንን ያጠኑ ነበር። (ቡኻሪ ዘግበውታል)
2️⃣. የጾም ወር (شهر الصيام)•አላህ እንዲህ ይላል፦ "እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደተደነገገው በናንተም ላይ ተደነገገ።" [በቀራህ፡ 183]
•ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ "የረመዳን ወርን በእምነትና ከአላህ ምንዳን በመፈለግ የጾመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።" (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
3️⃣. የበጎ አድራጎት ወር (شهر الخير)•ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከሰው ሁሉ ይበልጥ ቸር ነበሩ፤ ይበልጥ ቸር የሚሆኑት ደግሞ በረመዳን ወር ነበር። (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
•ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ "ጾመኛን ያስፈጠረ ሰው የጾመኛውን ያክል ምንዳ ያገኛል።" (አህመድ ዘግበውታል)
4️⃣. የለይለቱል ቀድርና የሶላት ወር (شهر القيام)•ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ "የረመዳን ወርን በእምነትና ከአላህ ምንዳን በመፈለግ (በሶላት) የቆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።" (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
•ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ "የለይለቱል ቀድርን ሌሊት በእምነትና ምንዳን በመፈለግ በሶላት የቆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።" (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
🔵 @TewhedandSuna ❤️