👉የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ፕሮጀክት እጩዎች ዝርዝር በዋናነት በቻይና ኩባንያዎች ተይዟል።

💫Chinese Firms Dominate Shortlist for Bishoftu Airport Project

🚧​የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ፕሮጀክት የዋና ሥራዎች የግንባታ፣ የግዥ እና የፋይናንስ (EPC-F) ጨረታ የቅድመ-ብቃት ግምገማን አጠናቆ ዓለም አቀፍ ጥምረት ያላቸውን ድርጅቶች በእጩነት መርጧል። ግሩፑ ውጤቱን ቅዳሜ ዕለት ያሳወቀ ሲሆን፣ የተመረጡት ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ቀርቦላቸው ወደ ቀጣዩ ደረጃ እንዲሸጋገሩ ይደረጋል።
​ፕሮጀክቱ በአራት ዋና ዋና ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን፣ እነሱም፡-
• ​F1: ዋና ዋና መገልገያዎች (Main Facilities)
• ​F2: የድጋፍ ሰጪ መገልገያዎች (Support Facilities)
• ​I1: የአየር ማረፊያ ሜዳ እና መሰረተ ልማት (Airfield and Infrastructure)
• ​I2: ከግቢ ውጭ ያሉ ትስስሮች (Offsite Links) ናቸው።
​ለዋና ዋና መገልገያዎች (F1) ፓኬጅ ሰባት ኩባንያዎች ያለፉ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል፡-
• ​ቻይና ኮሚዩኒኬሽንስ ኮንስትራክሽን ካምፓኒ (CCCC)
• ​በቻይና ኮንስትራክሽን ኤይትዝ (eighth) ኢንጂነሪንግ ዲቪዥን (CCEED) እና በቻይና ሮድ ኤንድ ብሪጅ ኮርፖሬሽን (CRBC) የተመሰረተ ጥምረት
• ​ቤጂንግ አርባን ኮንስትራክሽን ግሩፕ (BUCG) እና ሌሎች አራት ድርጅቶች ይገኙበታል።
​ለከግቢ ውጭ ትስስሮች (I2) ፓኬጅ ደግሞ በኢትዮ-ጂቡቲ ምድር ባቡር (EDR) እና በቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (CCECC) መካከል የተመሰረተ ጥምረት በእጩነት ከቀረቡት መካከል አንዱ ነው። በጥቅሉ ሲታይ በእጩነት ከተመረጡት ኩባንያዎች መካከል ግማሽ ያህሉ የቻይና ኩባንያዎች ናቸው።

Via Addis Fortune

@etconp

Comments

Be the first to add a comment