This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌱 እጃችንን ሲያሳክከን "ሲሳይ (ርዝቅ) ሊመጣልኝ ነው" ማለት ይቻላል ⁉️

• አንዳንድ ሰዎች እጃቸውን ሲያሳክካቸው "ሲሳይ (ርዝቅ) ሊመጣልኝ ነው" ይላሉ። አፍንጫቸው ሲያሳክካቸው ደግሞ "እንግዳ ሊመጣብኝ ነው" ይላሉ። የዚህ ዓይነቱ አባባል በኢስላም ያለው ብይን ምንድን ነው?

• ​ይህ ድርጊት በኢስላም "ትንሹ ሽርክ" ተብሎ ይመደባል። ምክንያቱም፡-
​አላህ (ሱ.ወ) በሸሪዓውም ሆነ በተፈጥሮ ሕግጋት (ቀደር) ምክንያት ያላደረገውን ነገር እንደ ምክንያት አድርጎ መውሰድ ስለሆነ።
​በሸሪዓውም ሆነ በተፈጥሮ ሕግጋት እጅን ማሳከክ ከሲሳይ መምጣት ጋር የሚያያይዝ ምንም ዓይነት መረጃ የለም።

•​ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
​"ተሚማህ (ክታብ ወይም ከክፉ ዓይን ለመከላከል የሚታሰሩ ነገሮችን) ያንጠለጠለ ሰው በእርግጥም አጋርቷል (ሽርክ ፈጽሟል)።" (ቲርሚዚ የዘገቡት ሶሂህ ሀዲስ)

•​ይህ የሆነበት ምክንያት፡-
​ተሚማህ (እንደ ዕንቁ ወይም ክር ያሉ ነገሮች) ከክፉ ዓይን ይከላከላሉ ተብለው ይታሰባሉ።
​አላህ ግን እነዚህን ነገሮች ለመከላከያነት በሸሪዓውም ሆነ በተፈጥሮ ሕግጋት ምክንያት አላደረጋቸውም።

🌱 @TewhedandSuna

Comments

Be the first to add a comment