ሰላም ጤና ይስጥልኝ በዚህ ወር ስለሀሰተኛ ሰነዶች አዘጋጅተናል መልካም ነባብ!
ክፍል 1
ሀሰተኛ ሰነዶችን መፍጠር፡-
ማለት ሕጋዊ ክርክሮች ሲካሄዱ በማስረጃነት የሚቀርቡ፤ አንድን ፍሬ ነገር ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ወይም የሚያረጋግጡ የሌላን ሰዉ የጣት ፊርማ፤ ፊርማ፤ ምልክት፤ ወይም ማህተም በመጠቀም እዉነተኛዉን ጽሁፍ በመለወጥ ወይም በመደለዝ፤ የሌላዉን ሥልጣን ወይም ችሎታ እንዳለዉ አድረጎ፡
- ጽሁፎችን
- ሌሎች ሰነዶችን
- ግዙፍ ነገሮች(የሚታይ፤ የሚዳሰስ፤ የሚጨበጥ) ማዘጋጀት ነዉ
ሰነዶችን ወደ ሐሰተኝነት መለወጥ፡-
አንድን ሰነድ፤ በተለይም የፈራሚዉን ስም ወይም ፊርማ ወይም የሰነዱን ይዘት፤ አሀዝ፤ ፍሬ ነገር ወይም ዝርዝር መግለጫ በሙሉ ወይም በከፊል በመለወጥ፤ በማሻሻል፤ በመቀነስ ወይም በመጨመር ወደ ሐሰተኛነት መለወጥ ነዉ፡፡
ሰነዶችን ማጥፋት፡-
በሌላ ሰዉ ሰነድ ላይ ጉዳት እንዲደርስበት ማድረግ፤ መቅደድ ጥቅም ላይ እንዳይዉል ማድረግ ወይም መዉሰድ ነዉ
አነዚህ ድርጊቶች የሚፈጸሙት
- የሌላዉን ሰዉ መብት ወይም ጥቅም ለመጉዳት አሊያም
- የድርጊቱ ፈጻሚ ለራሱ ወይም ለሌላ ሰዉ ተገቢ ያልሆነ ማናቸዉንም መብት ወይም ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት በማሰብ ነዉ፡፡
ይህ ደግሞ የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትል ሲሆን ተጠያቂነቱን በ3 ነገሮች ላይ ይመሰረታል
የመጀመሪያዉ፡- በሚፈጠሩት፤ በሚለወጡት ሀሰተኛ ሰነዶችን እና በነዚሁ መገልገል በጠቅላላዉ
ሁለተኛዉ፡- በሀሰት በሚፈጠሩት ወይም ወደ ሀሰት በሚለወጡት ሰነዶች አይነት እና
ሶስተኛዉ፡- የድርጊቱ ፈጻሚ አካል/ግለሰብ ማንነት ወይም ኃላፊነት ላይ ነዉ
ሕድአት ጌታቸዉ ሕ/ስ/ም/መ/ዳ/ዐቃቤ ሕግ

Comments

Be the first to add a comment