👉የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) አሁን ባለው የአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ 150 ክፍሎች ያሉት አዲስ ‘Hilton Garden Inn’ እና የጤናና ደህንነት ማዕከልን (Wellness facility) በ55 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ሊገነባ መሆኑን አስታወቀ።
ይህ ግንባታ አዲስ አበባ በህዳር ወር 2020 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ ኖቬምበር 2027) ለምታስተናግደው 32ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ የከተማዋን የእንግዳ ማስተናገድ አቅም ለማሳደግ ያለመ ነው።
ከተማዋ ለጉባኤው ከ80,000 በላይ የውጭ ልዑካንን የምትጠብቅ ሲሆን፣ አሁን ያላት የሆቴል መኝታ አቅም ግን 25,000 ገደማ ብቻ ነው።
በመሆኑም የዚህ አዲስ ሆቴል ግንባታ በፈረንጆቹ ኦክቶበር 2027 ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ታቅዷል።
የፕሮጀክቱ ስምምነት ዛሬ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አዲስ ዋና መሥሪያ ቤት የተፈረመ ሲሆን፤ የዲዛይን እና ግንባታ ሥራውን ‘ኤልሚ ኦሊንዶ ኮንትራክተርስ’ ተረክቦታል።
‘ዚያስ አርክቴክቸር እና ኢንጂነሪንግ’ ደግሞ የፕሮጀክቱ አማካሪ ሆኖ ተሰይሟል።
በተያያዘ ዜና ኤልሚ ኦሊንዶ ኮንትራክተርስ ከሆልዲንግሱ ጋር ያለው ስራ በዚህ ብቻ አላበቃም፤ ኢትዮጵያን የዓለም አቀፍ የአውትሶርሲንግ አገልግሎቶች መዳረሻ ለማድረግ ያለመና 3,000 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል የቢዝነስ ፕሮሰስ አውትሶርሲንግ ማዕከል በ25.56 ሚሊዮን ዶላር ለመገንባት የሚያስችል ተጨማሪ ስምምነት ተፈራርሟል።
ይህ የBPO ፕሮጀክት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማብዛት፣ የውጭ ምንዛሪ ለማስገኘት እና የመንግስት የልማት ድርጅቶችን አቅም ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅዖ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል።
@etconp