#TIGRAY

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው 316 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 31 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።

ከሰላሳ አንዱ (31) መካከል 21 የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 8 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሲሆኑ 2 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ናቸው።

#OROMIA

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 241 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 3 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

- 2 ሰዎች ከቡራዩ (የ 38 እና 30 ዓመት ወንዶች) ፤ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌላቸው፤ ከማህበረሰቡ የተገኙ።

- 1 ሰው ከአዳማ (የ38 ዓመት ወንድ) የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌለው፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

#AFAR

በአፋር ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 49 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተካሄደው የላብራቶሪ ምርመራ 66 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው። በክልሉ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 33 ደርሰዋል።

#DireDawa

በድሬዳዋ ከተማ አስተደር ከተካሄደው 96 የላብራቶሪ ምርመራ 2 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጧል። በቫይረሱ የተያዙት ሁለቱም ወንዶች ሲሆኑ ግለሰቦቹ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ናቸው። በድሬዳዋ አጠቀላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 15 ደርሰዋል፤ 8 ሰዎች አገግመዋል።

@TenaET

Comments

Be the first to add a comment