"የተሳሳተ መረጃ ነው" መሬት አስተዳደር

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ባወጣው መግለጫ በቅርቡ "የመሬት ጉዳይ በከንቲባዋ ብቻ እንድወሰን ተገደበ" በሚል የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው ብሏል።

ሚድያዎች መረጃዎችን ከምንጩ ሳያረጋግጡ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ከማሰራጨት እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ያስተላለፈው ውሳኔ በመሬት አስተዳደር ዘርፍ የሚታዩ ቢሮክራሲያዊ እንግልቶችን እና መዘግየቶችን ማስቀረት እንጂ ከመሬት አሰጣጥ ደንብ ወይም መመሪያ ውጭ የወጣ አይደለም ብሏል።

የካቢኔ ስብሰባን በመጠበቅ ፋንታ ሕጋዊ ይዞታዎች እንዲከፈሉ የሚቀርቡ ጥያቄዎች ሂደትን በማሳጠር በመሬት አስተዳደር ቢሮ ተረጋግጦ በከንቲባ ጽሕፈት ቤት ፀድቆ እንዲፈጸም የሚያስችል አሠራር ነው።

ውሳኔው ሕብረተሰቡን ሊያደናግር በማይገባ መልኩ የተዛባ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑ ተገልጾ፣ ሕብረተሰቡ በደላሎች ወሬና ባልተረጋገጠ መረጃ እንዳይደናገር ጥሪ አቅርቧል።

@etconp

Comments

Be the first to add a comment