👉የመንገድ ግንባታ ዋና ደረጃዎች (Main Stages of Road Construction)
🚧መንገድ ግንባታ በየደረጃው በጥንቃቄ የሚከናወን ሥራ ሲሆን እያንዳንዱ ደረጃ ለመንገዱ ጥንካሬ፣ ዘላቂነት እና ደህንነት ትልቅ ሚና አለው።
1. የሳይት ዝግጅት (Site Preparation)
ዛፎች፣ቁጥቋጦዎች እና ሌሎች እንቅፋቶችን ማስወገድ (Clearing & Grubbing)
የመንገዱን አቅጣጫ እና ወሰን በሰርቬይ መወሰን (Setting Out)
የግንባታ ቦታውን ለስራ ዝግጁ ማድረግ
2. የመሬት ሥራ (Earthwork)
ከፍ ያለ ቦታ መቆፈር (Cut)
ዝቅተኛ ቦታ በአፈር መሙላት (Fill)
አፈሩን በኮምፓክተር ማጠናከር (Compaction)
የመንገዱን Formation Level ማዘጋጀት
3. ሳብግሬድ (Subgrade)
ይህ የመንገዱ መሠረታዊ የአፈር ክፍል ነው።
ሁሉንም የላይኛ ንብርብሮች የሚሸከም መሠረት ነው።
በትክክል ካልተኮምፓክት መንገዱ በፍጥነት ሊበላሽ ይችላል።
4. ሳብ-ቤዝ (Sub-base)
በ Subgrade ላይ የሚቀመጥ የጠጠር ወይም የተፈጨ ድንጋይ ንብርብር ነው።
ጭነትን በስፋት ያሰራጫል።
የውሃ ፍሳሽን ያሻሽላል።
5. ቤዝ ኮርስ (Base Course)
የመንገዱ ዋና ጭነት ተሸካሚ ክፍል ነው።
የተሽከርካሪዎችን ክብደት ወደ ታችኛው ንብርብር ያስተላልፋል።
ከተፈጨ ድንጋይ (Crushed Aggregate) ይሠራል።
6. ባይንደር ኮርስ (Binder Course)
በBase Course እና Wearing Course መካከል ያለ የአስፋልት ንብርብር ነው።
ንብርብሮቹን እንዲጣበቁ ያደርጋል።
ተጨማሪ ጥንካሬ ይሰጣል።
7. ዌሪንግ ኮርስ (Wearing Course)
ይህ ተሽከርካሪዎች በቀጥታ የሚንቀሳቀሱበት የመንገዱ የላይኛው ክፍል ነው።
ለስላሳ ጉዞ ይፈጥራል።
የጎማ መንሸራተትን ይቀንሳል።
መንገዱን ከፀሐይ፣ ከዝናብ እና ከሌሎች የአየር ሁኔታዎች ይጠብቃል።
8. ሾልደር እና ድሬኔጅ (Shoulder and Drain)
ሾልደር (Shoulder) በመንገዱ ጎን የሚገኝ ክፍል ነው።
ለአደጋ ጊዜ ማቆሚያ ይሆናል።
የመንገዱን ጠርዝ ይደግፋል።
ድሬኔጅ (Drainage) ደግሞ የዝናብ ውሃን ከመንገዱ ለማራቅ ይጠቅማል።
9. የመንገድ ምልክቶች እና መሳሪያዎች (Road Markings and Furniture)
የመስመር ምልክቶች (Lane Markings)
የትራፊክ ምልክቶች (Traffic Signs)
ጋርድሬል (Guardrails)
የመንገድ መብራቶች (Street Lights)
እነዚህ ሁሉ ለመንገድ ተጠቃሚዎች ደህንነትና ትራፊክ ቁጥጥር አስፈላጊ ናቸው።
💫አጠቃላይ የRoad Pavement Layer ቅደም ተከተል
Wearing Course
⬇️Binder Course
⬇️Base Course
⬇️Sub-base
⬇️Subgrade (Compacted Soil)
@etconp