የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
ይህንን ያውቁ ኖሯል?
በየጊዜው በምናደርገው የግብይት እንቅስቃሴ ውስጥ የውል ስምምነት እያደረግን ቢሆንም በፍትሀ-ብሔር ሕጎችን ለውል መመስረት አስፈላጊ የሆኑ መስፈርቶችን ማወቅ አለብን ፡፡
1/ የተዋዋይ ወገኖች ችሎታ፡- (የተፈጥሮ ሠው ወይም የህግ የሰውነት መብት የተሠጠው አካል ) በህግ ፊት ውጤት ያለውን ተግባር ለማከናወን ያለውን ብቃት የሚመለከት ነው።
2/ የተዋዋይ ወገኖች ነጻ ፍቃድ፡- አንድ ውል በሕግ ፊት የሚፀና እንደሆነ ተዋዋይ ወገኖች ነፃ ፍቃዳቸውን የገለጹበት መሆን አለበት።
3/ የውለታው ጉዳይ ፡- ለውሉ መመስረት ምክንያት የሆነ ነገር ወይም ጉዳይ ሕጋዊ፣ ሊፈፀም የሚችል እና ለሞራል ተቃራኒ ያልሆነ መሆን ይገባዋል።
4/ የውሉ አቀራረፅ (ፎርም) ከሌሎች ውሎች በተለዬ ሁኔታ ሕጉ ልዩ አቀራረፅ (ፎርም)የሚጠይቅ ከሆነ በዛው መሠረት ብቻ መሆን አለበት።
እነዚህን ከላይ የተጠቀሱ መሰረታዊ ጉዳዮች በፍትሐ-ብሔር ሕግ አንቀፅ 1678 ላይ የተገለፁ ሲሆን በዚሁ መሠረት አውቀን መጠቀም አለብን።
ጥቅምት 17 ቀን 2015 ኣ.ም
አሊ ሳፊ የሕ/ስ/ም/መ አቃቤ ሕግ
Comments
Be the first to add a comment