በፌደራል ጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥ እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1249/2013 አንቀጽ 5 መሠረት የሚከተሉት አካላት የጥብቅና ፍቃድ ሳያስፈልጋቸው የጥብቅና አገልግሎት መስጠት ይችላሉ፡-
1. ስለራሱ ጉዳይ የሚከራከር ሰው፤
2. ያለክፍያ ለትዳር ጓደኛው፤ ለወላጁ፤ ለልጁ፤ ለአያቱ፤ ለእህቱ፤ ለወንድሙ፤ ለትዳር ጓደኛው ወላጆች፤ እንዲሁም ሞግዚት ወይም አሳዳሪ ለሆነለት ሰው የሚከራከር ሰው፣
3. ከሥራው ጋር በተያያዘ ጉዳይ የሚከራከር ዐቃቤ ሕግ፣
4. ሕጋዊ ሰውነት ባለው የንግድ ድርጅት፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት፤ ሕዝባዊ ድርጅት፣ የሃይማኖት ተቋም፣ የሙያ ማኅበር፣ ዓለም አቀፍ ድርጅት ወይም በሌላ አግባብነት ባለው ሕግ መሠረት በተቋቋመ ድርጅት ተቀጥሮ የተወከለ ሰው፣
5. የመንግስት መሥሪያ ቤትን ወይም የልማት ድርጅትን በሚመለከት የሚከራከር ማንኛውም የመንግስት መሥሪያ ቤት ወይም የልማት ድርጅት ባለስልጣን ወይም ኃላፊ ወይም በእርሱ የተወከለ ሰው፣ ወይም
6. ማንኛውም የሠራተኛ ማኅበር መሪ ወይም ማህበሩ የሚወክለው ሰው፡፡
ኦምኒኤል (ህዳር 30/03/2014 ዓ.ም)

Comments

Be the first to add a comment