የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
እንደስም ማጥፋትና ስድብ ያሉ የወንጀል ጉዳዮች በፌዴራል ፍርድ ቤቶች መታየታቸው ቀረ
ሐምሌ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በግል አቤቱታ አቅራቢነት ክስ የሚመሠረትባቸው የወንጀል ጉዳዮች እና በግለሰቦች መካከል የሚደረጉ እስከ ብር 500 ሺ የገንዘብ፣ ውልና ብድር የፍትሐ ብሄር ጉዳዮች በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና በፌዴራል ፍርድ ቤት መታየታቸው ቀርቶ በአዲስ አበባ ከተማ እና በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ዐቃቤ ሕግ ቢሮ እና ፍርድ ቤቶች መታየት ይጀምራሉ፡፡
በዚህም ምክንያት ከተጠቀሰው እለት አንስቶ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እነኚህን ጉዳዮች ተቀብሎ የማያስተናግድ በመሆኑ እንደ ስድብ፣ ስም ማጥፋት፣ ዛቻ እና ሌሎች ቀላል እና በተበዳዩ አቤቱታ መሰረት ክስ የሚያስመሰርቱ ጉዳዮች እንዲመረመሩለት የሚፈልግ ወይም የዋጋ ግምቱ ከ500 ሺ ብር በታች የሆነ የፍትሀብሄር ክስ ማቅረብ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው አቤቱታውን ወንጀሉ የተፈጸመበት ቦታ ለሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ወይም ለከተማ አስተዳደሩ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ እና ፍርድ ቤት እንዲያቀርብ አሳስቧል።
Comments
Be the first to add a comment