የቦሌ ክ/ከተማ የሕግ ስርፀትና ምክር መስጠት ዳይሬክቶሬት
ጤና ይስጥልኝ!
መቸም ብዙ ይገጥማልና መካሰስን እንዲያርቅለወት ልባዊ ምኞቴ ነው፡፡!
በዚች መልእክት እታዲያ በፍትሐብሄር ስነስርዓት ክስ ሲገጥመወት ምንምን መቃወም እንዳለበወት በስነስርዓትሕጉ የተደነገገውን ይኸው!!!
በመጀመሪያ ደረጃ ክርክር ላይ ስለሚቀርቡ መቃወሚያዎች፡፡
1. ማስረጃ ተቀብሎ ከመመርመሩ ወይም ምስክሮችን ከመስማቱ አስቀድሞ ፍርድ ቤቱ በመጀመሪያ ደረጃ ለቀረበለትና ማናቸውም ተከራካሪ ወገን ላቀረበው መቃወሚያ ውሳኔ መስጠት አለበት፡፡
2. ማናቸውም ተከራካሪ ወገን ከዚህ ቀጥሎ የተመለከተውን መቃወሚያ በሚያቀርብበት ጊዜ በዚህ ሕግ በቍጥር 245 የተነገረው ድንጋጌ ተፈጻሚ የሚሆነው፤
ሀ/ ፍርድ ቤቱ ነገሩን ለመስማት ሥልጣን የለውም በማለት መቃወሚያ ሲያቀርብ፤
ለ/ ክስ የቀረበበት ጉዳይ አስቀድሞ በፍርድ የተወሰነ መሆኑን የሚገልጽ መቃወሚያ ሲቀርብ፤
ሐ. ክስ የቀረበበት ጉዳይ በሌላ ፍርድ ቤት ቀርቦ በክርክር ላይ ያለ መሆኑን የሚያስረዳ መቃወሚያ ሲቀርብ፤
መ. አንደኛው ተካራካሪ ወገን በነገሩ የማያገባው መሆኑን በመግለጽ በጉዳዩ ውስጥ ገብቶ መከራከር አይገባውም በማለት መቃወሚያ ሲቀርብ፤
ሠ. ክሱ በይርጋ የታገደ መሆኑን የሚገልጽ መቃወሚያ ሲቀርብ፤
ረ. ወይም ክሱ የተነሳበት ነገር በሽምግልና ታይቶ በስምምነት የተፈጸመ መሆኑን ወይም ለእርቅ የተቀጠረ መሆኑን የሚገልጽ መቃወሚያ ሲቀርብ ነው፡፡
3. በዚህ ቁጥር እንደተነገረው የቀረቡት መቃወሚያዎች ከአንድ በላይ ሲሆኑ በተቻለ መጠን በቶሎ ተጠቃለው ሁሉም መቅረብ አለባቸው፡፡ መቅረብ ከሚገባቸው መቃወሚያዎች ውስጥ ሳይቀርቡ የቀሩት ትክክለኛውን ፍርድ ለመስጠት የማያሰናክሉ ከሆኑ ባለጉዳዩ ራሱ ሆነ ብሎ ለማቅረብ ባለመፈለግ እንደተዋቸው ይቆጠራሉ፡፡
4. ባንድ ክስ ውስጥ የተያዘው ጭብጥ ለየራሱ ፍሬ ነገርንና ሕግን የሚመለከት በሆነ ጊዜ ፍርድ ቤቱ የሕጉን ጥያቄ በመከተል ክሱን በከፊል ወይም በሙሉ ለመወሰን የሚችል ሲሆን በመጀመሪያ በሕግ ጉዳይ ለተያዙት ጭብጦች ውሳኔ መስጠት አለበት፡፡ ተገቢ ሆኖ ሲያገኘውም በሕግ ረገድ የተያዙትን ጭብጦች እስኪወስን ድረስ በፍሬ ነገር የተያዘውን ጭብጥ በቀጠሮ ሊያቆየው ይችላል፡፡
መጋቢት 8/2014 ዓ.ም(ሲሳይ ሰማኝ)
Comments
Be the first to add a comment